Get Mystery Box with random crypto!

ለካስ ቀን ይመጣል ከፊሊሞና ረቂቅ ቃላትን ላንተ ሰባጥሬ መፅሀፍ ቅዱሱን ከፊቴ ደንቅሬ ከ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ለካስ ቀን ይመጣል
ከፊሊሞና

ረቂቅ ቃላትን ላንተ ሰባጥሬ
መፅሀፍ ቅዱሱን ከፊቴ ደንቅሬ
ከበራፍህ ቆሜ ፀሎት አድርሻለው
ስጋና ደምህን በአፌ ቀምሻለው
ሀጢአቴን እንዳብስ ላንተ ሰግጃለው ።
ፀበል ተጠምቄ ትዕዛዝን አክብሬ
ለእምነቴ ፅኑ ታምኜ ለክሬ
ቆሜ አለው ከደጅህ ምላሽ እንድትሰጠኝ
ላደረስኩት ፀሎት መልሱን እንድትነግረኝ።

ፀሎቴ ደረሰህ ምላሽ ስጠኝ ጌታ
ሞት እንዳይቀድመኝ አለምን ሳልረታ
ግን
ለሁሉም ጊዜ አለው
ለካስ ቀን ይመጣል
ፀሎቴም ይደርሳል ።

አሜን ።

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19