🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

የፍቅር መድረሻው! (አኑ) ሂድ ስትለው መጣ፣ ውረድ ሲባል ወጣ፣ ውጣ ሲባል ሲወርድ፣ አንዴ እሷን | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

የፍቅር መድረሻው!
(አኑ)

ሂድ ስትለው መጣ፣
ውረድ ሲባል ወጣ፣
ውጣ ሲባል ሲወርድ፣
አንዴ እሷን ሲጠላ ፣ አንዴ ደግሞ ሲወድ፣
ከራሱ ተጣልቶ፣
ከራሱ ተኳርፎ፣
ነብሱን ይረግማታል በአንዲት ሴት ተለክፎ

(ያቺ ሴት)

የሆነ ዘመን ላይ ፍቅረኛው ነበረች
በፍቅሩ የከነፈች፣
ስለሱ የምትኖር፣ ስለሱ የምትሞት!
እሱም የሚያፈቅራት
ከጎና ማይጠፋ
ፍቅር እንደማግኔት ከሷ ጋር አጣብቆት!
አንድ'ዜ በሀይቅ
አንድ'ዜ በየብሱ
አንድ'ዜ በአየር
ፍቅርን ሸክፈው ሲንሳፈፉ ነበር።

(ዛሬ)

ተጣልተው
ተኳርፈው
ደግሞም ተለያየተው
አንድ ፍቅራቸውን ሁለት ቦታ ከፍለው
ጎጆውን አፍርሰው
ተነጣጥለው አሉ
ትላንትን ታቅፈው እንዲኹ ይኖራሉ።

(እሱ)

ጎዳና ዳር ካለ አንድ ካፌ ገብቶ
ለካፌ አሳላፊው ፣ አዞ ማኪያቶ
( ሁለት ነው ያዘዘው)
አንደኛው ለራሱ
ሁለተኛው ደግሞ ለሄደች ፍቅሩ
እርግጥ ነው የለችም
በምዕናብ ሊያኖራት ከባዶ ወንበሩ
(እንዲኽ ነው ሀሳቡ)

ትዕዛዙ እስኪመጣ
ጋዜጣ ያነባል
የጋዜጣው ርዕስ
ጥያቄ ይጠይቃል

(ጥያቄው)
ከአላህ እና ከእግዜር የቱ ነው ትክክል?
ከርዕሱ በታች
የቄስና የሼኽ የፈገግታ ምስል ፣

(እዚህ ጋር)

ቄሱም ሆነ ሼኹ
የፃፉትን ፅህፈት፣
የሰበኩት ስብከት፣
ካነበበ ኋላ ደረሰ ከእውነት!

(እውነቱ)

የቄሱም የሼኹም
የኣላህም የእግዜሩም
ቃሎች ሲመረመር
ፍቅር ነው መነሻው፣ ፍቅር ነው መድረሻው፣
ከፍቅር ለራቀ
የይቅርታ ቃል ነው መምጫ መመለሻው፣

( ያዘዘው ማኪያቶ ከመጣ ቆይቷል
ጋዜጣ ሲያነብ ረስቶት ቀዝቅዟል)

ሳይጠጣው ተነሳ
ጋዜጣውን ይዞ መንገዱን ጀመረ
ሚጓዝበት መንገድ
ማይሽር ፣ የማይጠፋ
ከአንዲት ፍቅሩ ጋራ ትዝታ ነበረ።
እርምጃው ፈጠነ
ይሄዳል ፣ ይሄዳል ፣ ይሄዳል ፣ ይሄዳል
ፍቅሩ ቤት ደረሰ ፣
በሯን ደበደበ፣
እየሮጠች ወጣች፣
የበፊት ህይወቷ ፊትለፊቷ ቆሟል
የምትለው ጠፋት
ፍርሀት ነብሷን ዋጣት


ሱ...

ተንበርክኳል
እግሯ ስር ተገኝቷል
በስስት ፣ በፍቅር
ሽቅብ አይኗን ያያል
ይቅርታ የሚል ቃል
ከአንደበቱ ይፈልቃል




አለቀሰች
አይኗን እንባ ወረሰው፣
አካላቷን ሙሉ ደስታ አንቀጠቀጠው፣

ተነሳ አቀፈቹ
ሲያያት ሳመቹ









አለች
እየሳቀች

ጋዜጣውን አየ

ፍቅር ነው መነሻው ፣ ፍቅር ነው መድረሻው ፣
ከፍቅር ለራቀ
የይቅርታ ቃል ነው መምጫ መመለሻው፣

ይኽን አስታውሶ
ፊቱን ብርሀን ሞላው።


@anu_yesua

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19