🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ጅብና አህያ ከአንድ ዱር ማዶ ካረፈ መስክ ላይ ከምስኪን ገበሬ ቤት ከተራራው በላይ አንዲት አህያ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ጅብና አህያ

ከአንድ ዱር ማዶ ካረፈ መስክ ላይ
ከምስኪን ገበሬ ቤት ከተራራው በላይ
አንዲት አህያ ውስጧ የተራበ
በእህል ውሀ እጦት አንጀቷ የጠበበ
ውብ ለአይን ሚገባ ምግብ ተመልክታ
እየሮጠች መጣች ከባለቤቷ ጠፍታ
እንደደረሰችም ከለምለሙ ሳር
ፈጠን ፈጠን ብላ መጋጥ ብጀምር
ካላስተዋለችው ከዱሩ ውስጥ ፈጥኖ
አያ ጅብ ወጣና አናገራት ቀርቦ
ወዳጄ አህያ እንደምን ከርመሻል
ከሰው ልጅ ጋር መኖር እንዴትስ ይዞሻል
ደግሞ ከተያየን ትንሽ ቆየን አይደል
ምን እግር ጣለሽ ባለቤትሽስ የታል
ደህና ነኝ አያ ጅብ ኑሮም ተስማምቶኛል
ከተገናኘንም ወራቶች አልፎናል
ከቤቴ አቅራቢያ ሳለው ተቀምጬ
አሻግሬ ሳይ ወደዚህ አፍጥጬ
ከምግብ የራቀው ሆዴ ሞረሞረኝ
ለምለሙን ሳርም ሳይ አላስችልሽ ቢለኝ
ቀስ ብዬ ወጣሁ ከምኖርበት
ማንም ሳይከተለኝ መጣሁ በፍጥነት
ልክ እንደሷ ሁሉ ለቀናት ከምግብ የራቀው
የአያ ጅብ ጆሮ ሲሰማ ደስ አለው
ከተራብሽ እንዲህማ ጥሩ ግብዣ ነበረኝ
ከዋሻ እንሂድና በአይነት በአይነቱ ልስጥሽ ደስ እንዲለኝ
ምንም አላቅማማች በሀሳቡ ተስማማች
በረሀቧ ብዛት ጅብ መሆኑን ረሳች
ከቤቱም ደረሱ ወደ ግብዣው መንደር
ሞኝዋ አህያ እውነት መስላት ነበር
ትንሽ ሳር ጥሎላት እሱን ስትበላ
ረሀቡ ያላስቻለው ጋባዧ ከኋላ
ራስሽን አስበላሽ አንቺ ጅል ፍጥረት
ብሎ ሰፈረባት ሆዱን ሞላባት
እበላለው ብላ አህያ ተበላች
ምግብን ፍለጋ ጠላቷን ዘነጋች።

24/04/14
ሰላም (Selito)

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19