🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

. ተስፋ አድርግ ይሉኛል መውደቄ ገርሟቸው ራቴን ለመግዛት ተስፋየን እንደሸጥኩ ማን በነገራቸው | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

.

ተስፋ አድርግ ይሉኛል መውደቄ ገርሟቸው
ራቴን ለመግዛት
ተስፋየን እንደሸጥኩ ማን በነገራቸው

አትድፋው ይሉኛል ገርሟቸው መድፋቴ
ከባዶ ሆዴ ጋር
ጨዋታ እንደያዝኩኝ መች አውቀውት እቴ

ገረማቸው ከልብ ኮነኑት ማልቀሴን
በእንባ ካላጀብኩት
የየት ሀገር ዳኛ ይሰማኛል ክሴን

በዋርካ ስር ቆሜ እንዲ 'ምወራጨው
በሽማግሎች ፊት በብሶት ምጮኸው
ዝም ካልኩ ዝም ነው ብየ አስቤኮ ነው

ሰረቁና ሳቄን
ደራረቡት ማቄን
ከጄ ነጥቀው በልተው
ከአልጋየ ተኝተው
እውነቴን አሳስተው ተንቀባረሩብኝ
ጭራሽ ደሞ ብሶ
ተራብኩኝ አትበል
እንቅልፍ አጣሁ አትበል
ፍትህ የለም አትበል ብለው ጨከኑብኝ

ጨክኜ ያለፍኩትን ያንን ጎዳናየን
ለሰው እያወሱ ያለፈ ጥላየን
ሲከሱኝ ዝም ባልኩኝ
ሲዘልፉኝ ባለፍኩኝ
መጠየቅ የማላውቅ የደላኝ መሰልኩኝ

አትፈርዱም አውቃለሁ ብቻ ስሙኝ ድምፄን
ከተራ አትቁጠሩት አትጣሉ አመፄን
ዘራፍ!
ዘራፍ!
ዘራፍ!
ዘራፍ አልልበት በምኔ ላይ ቆሜ
እንዴት ልራመደው ሆዴ ላይ አቂሜ

አሸልቤ እያለሁ ባልነቃ ደግሜ
አረፍ እንዳልኩበት ብቀር ተጋድሜ
ገዳየን ፍለጋ ማዞር አልመኝም
ከሆዴ በስተቀር ጠላትስ የለኝም

እንዴት ያረጉታል
የኑሮን ውጥንቅጥ የሆድን ክርክር
አለስልሰው አያልፉት በቁጣ በምክር
ቀን ባነሳት ሀገር እኔን ቀኔ ጥሎኝ
ጧት ማታ ሸንጎ ስር ሆዴ ክስ አውሎኝ

ዘራፍ አልልበት በምኔ ላይ ቆሜ
እንዴት ልራመደው ሆዴ ላይ አቂሜ


በአቤኒ የተፃፈ


ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19