Get Mystery Box with random crypto!

አንቺን መውደድ ማለት.... እንደ መመነን ከ መካ ጠጠር እልፍ እንደ መዝገን እንደ መናገር የጌታን | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ


አንቺን መውደድ ማለት....
እንደ መመነን
ከ መካ ጠጠር እልፍ እንደ መዝገን
እንደ መናገር የጌታን ልሳን
...ንፁህ ነው!

አንቺን መውደድ ማለት...
በዝናብ ተመቶ_እሳት እንደ መሞቅ
ሆድ የባሰኝ ለታ ከ እናት እቅፍ መውደቅ!
አይነት ስሜት አለው

አቅፌሽ ባልነጋ ግዜ ባልቆጠረ
እጅሽን እንደያዝኩ
ጠረንሽ ዘላለም ከላዬ በኖረ...
ብዬ እመኛለው
እወድሻለው

ዳዊት ጌታቸው

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19