Get Mystery Box with random crypto!

የ12ኛ ክፍል ሀገርአቀፍ ፈተና ዉጤትን ከዛሬ ለሊት ጀምሮ መመልከት ይቻላል ለ2014 ትምህርት | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

የ12ኛ ክፍል ሀገርአቀፍ ፈተና ዉጤትን ከዛሬ ለሊት ጀምሮ መመልከት ይቻላል

ለ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት የተለቀቀ በመሆኑ ተፈታኞች ከዛሬ ጥር18 2015 ዓ.ም ከሌሊቱ 5፡30 ጀምሮ
• በዌብ ሳይት https://eaes.edu.et/

• በ6284 አጭር የጽሑፍ መልዕክት መላኪያ ላይ የምዝግባ ቁጥራቸውን (Registration Number) ብቻ በመላክ ወይም

• በቴሌግራም ላይ https://t.me/eaesbot
መመልከት ትችላላችሁ ሲል የትምህርት ሚኒስቴር አስታዉቋል፡፡

ሚኒስቴሩ አክሎም ፤ ማንኛውም ቅሬታ ያላቸው ተፈታኞች በአካል መምጣት ሳያስፈልግ እስከ ጥር 26/2015 ዓ.ም ድረስ በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዌብ ሳይት https://eaes.edu.et/ ላይ Compliant የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ቅሬታቸዉን ማቅረብ ይችላሉ ብሏል፡፡

በተጨማሪም ተማሪዎች የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አድራሻ ላይ ብቻ ይጠቀሙ የተባለ ሲሆን ከተመሳሳይ እና የተዛባ መረጃ ለማሰራጫት ከሚሞክሩ አካላት ይጠንቀቁ ሲል የትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል፡፡