Get Mystery Box with random crypto!

ከ እቅፌ ስትርቂ በረሀ መሀል ለይ ብቻውን የቆመ ንፋስ የገረፈው አሸዋ የቃመ ዘንባባ መስላለው። ት | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ከ እቅፌ ስትርቂ
በረሀ መሀል ለይ ብቻውን የቆመ
ንፋስ የገረፈው አሸዋ የቃመ
ዘንባባ መስላለው።
ትተሽኝ ስትሄጂ...
ከ ጎረምሳ መዳፍ እንደገባች እንስት
እጇ ተጠምዝዞ እንደምታቃስት
ኩሏ የረገፈ በትኩስ እንባዋ(አዬ መከራዋ)
እሷን እመስላለው
ብቻዬን ሆናለው።
በል ቻዎ ስትይኝ....
ትላንትና ወዲያ ጨምድደሽ የጣልሽው
የማስቲካ ሽፋን ንፋስ የወሰደው
እሱን እመስላለው....
ብቸኛ ዘንባባ
የተደፈረች ሴት ሆዷ ብዙ የባባ
ማደሪያ የሌለው የማስቲካ ሽፋን
እነሱ እና እኔ ምን ልዩነት አለን!!!!
ዳዊት ጌታቸው
Contact me @addemiinilik
19_05_2015

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19