🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ለአስተርዕዮ... (ታደሰ ደምሴ) አይኖችሽ... ወገግ ብለው ሲበሩ ሰላምን የሚዘምሩ ጥርሶችሽ፣ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ለአስተርዕዮ...
(ታደሰ ደምሴ)

አይኖችሽ...
ወገግ ብለው ሲበሩ
ሰላምን የሚዘምሩ

ጥርሶችሽ፣
ተላቀው ፈገግ ሲሉ
ሀሴትን ይመግባሉ

ልሳንሽ፣
ሲበዛ ለጀሮ ጣዕም
ተሰምቶ አይሰለችም!

ሌላ ሌላሽ ሁል ውብነው...
ስለልብሽ ምንም አልልም እግዜሩ ብቻ ይወቀው

ግና...
እግርሽ ግን መሔጃን አይመርጥም
በድሎት መንገድ ሲመራሽ ስለኔ ግድ አይለውም!

በይ እቴ...
በጌታ ፈቃድ  አንጾ በእውነት አይን ለተከተለው
ለአለም ለተተውን ፍጥረቶች ጽድቃችን ፍቅር ብቻ ነው!

በይ እቴ..
ረጅም ቀሚስ አጥልቀሽ
በጀርባ ዳዊት አንግተሽ

ነጭ ነጠላ ደርበሽ ወደ አስተርዕዮ ስትወጭ
የበዓሉ ወግ ከገባሽ ቅድሚያ ከኔ ዘንድ ተገለጭ!

#ሼርርር

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19