🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

(ካ..ል..ቆ..ሰ..ሉ) ============ አምላክ... ፍቅርን አፍላ ችግኝ የእለት ዘር ቢያደ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

(ካ..ል..ቆ..ሰ..ሉ)
============

አምላክ...
ፍቅርን አፍላ ችግኝ
የእለት ዘር ቢያደርገው
ውሀ አልሻ ብሎ
በአልቃሽ አፍቃሪዎች
እምባ ነው የሚያድገው  !

አምላክ...
ፍቅርን እንደመሬት
ለፍሬ ቢመርጠው
ይበልጥ ተቀዶ ለቆሰለ ሰው ነው
አብዝቶ ሚሰ'ጠው

አምላክ ....
ፍቅርን እንደ ጅረት
ዝቅ አርጎ ቢያፈሰው
ክብሬን ሳይል ቁልቁል ያዘነበለ ነው
ጠጥቶ ሚርሰው
:
ታዲያ
ከእኔነት ከፍታ ሳይንከባለሉ
ከመታበይ ዳገት ቁልቁል ሳይጣሉ
ተገፍተው ተረግጠው ዘምበል ሳይሉ
መች ቤቱን ሊሰራ
መች በዋዛ ሊገኝ
ፍቅር በቀላሉ
በሰው ካ..ል..ቆ..ሰ..ሉ  !

#kiyorna

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19