🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ብዙ ጠበቅሁሽ ከአንች በላይ ሰው የሌለ ይመስል። በናፍቆትሽ ተቃጥየ በትዝታሽ ስከስል። መመገብ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ብዙ ጠበቅሁሽ

ከአንች በላይ ሰው የሌለ ይመስል።
በናፍቆትሽ ተቃጥየ በትዝታሽ ስከስል።

መመገብ አቅቶኝ ዉሀው ሲጠማኝ።
ጉልበቴ ዝሎ አቅሜን ሲቀማኝ።

ሰው ማየት ከብዶኝ ልቤ ተሰብሮ።
አልድንም ሲለኝ ውስጤ ተመክሮ።

መራመድ ሲያቅተኝ ኑሮ ሲያስጠላኝ።
ፍቅርሽ ሳት ሆኖ ነዶ ሲበላኝ።

ታግሸ ስጠብቅ ያን ሁሉ ጊዜ።
ተስፋ ቆርጨ ስፅፍ ኑዛዜ።

ቀርተሽ ነበረ ጨክነሽ በእኔ።
የራቀኝ መስሎሽ ፈጣሪ ከኔ።

እኔም በፅናት ተማፀንኩና ለእሱ ነግሬ።
ፈውሱን ልኮልኝ ቢያቆመኝ በእግሬ።

ከልቤ ዙፋን ፈልቅቆ ቢያወጣሽ።
ምን አስበሽ ነው ሳገግም መጣሽ።?

ከሜ ዳውድ

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19