Get Mystery Box with random crypto!

አንዳንድ ቀን አለ... ጸሐይ ከዳተኛ ጨረቃ ሸንጎኛ ክዋክብት ቃል አባይ ለሰላለት እንጂ ለኔ ቢጤ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

አንዳንድ ቀን አለ...
ጸሐይ ከዳተኛ
ጨረቃ ሸንጎኛ
ክዋክብት ቃል አባይ
ለሰላለት እንጂ
ለኔ ቢጤ ትሁት ጎህን የማያሳይ!

ወጠጤ ጨለማ
ምርኩዝ ከእጅህ ነጥቆ  ሰካራም ካረገህ
ከለጋ አንገትህ ላይ
ሀሴትን የሚነጥቅ ዶፍ ካዘነበብህ

ሰማይ ስትሸሽህ
ምድር ስትተፋህ
ማት የመታው ዘመን
   ቀንህን ሲያጠለሸው
በያልፋል መወድስ
  ፈገግ ብለህ ሸኘው!!!


ታደሰ
ደምሴ

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19