Get Mystery Box with random crypto!

መምህር ማስተማር እንደዚህ ከሆነ ይቅርብኝ ፣ በአፌ መለምታ ከሚታመሙብኝ፣ መጥፎ ተናግሬ ከሚሰበ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

መምህር

ማስተማር እንደዚህ ከሆነ ይቅርብኝ ፣
በአፌ መለምታ ከሚታመሙብኝ፣
መጥፎ ተናግሬ ከሚሰበሩብኝ፣
ይቅር ማስተማሬ ይቅርብን ይቅርብኝ።
ድንቄም አስተማሪ ድንቄም መምህር፣
ጆሮውን ጠርቅሞ አፉን የሚያሾር።
ሞራልን ሰባብሮ አሟጦ አሻልቆ፣
የተነሳሳን ልብ አውድሞ አድቆ፣
መምህር አይደለም ካልተገኘ ልቆ፣
የተማሪን ችግር ካልተረዳ አውቆ፣
እርሱ እራሱ ችግር የትምርት ማነቆ፣
ካፖርቱን አስቀምጦ ይውጣ ክፍሉን ለቆ፣
ማስተማር ካልቻለ ጥሩ ሃሳብ አፍልቆ።
እኔ እስከማውቀው እስከሚገባኝ፣
መምህር አይን ነው ሁሉን የሚያስቃኝ።.....ግንሳ
ከተማሪ አንሶ ወርዶ ከረከሰ፣
የትውልዱን እንባ ቀርቦ ካላበሰ፣
ምኑን አስተማረ ምኑን አቋደሰ።


ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19