Get Mystery Box with random crypto!

ደመና እና ኮከብ በአንድ ሳር ሲበቅሉ አገር ጤዛ መስላ ጠዋት ትዘንባለች በሌሊት ሲውሉ፣ ምንም | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ደመና እና ኮከብ
በአንድ ሳር ሲበቅሉ
አገር ጤዛ መስላ
ጠዋት ትዘንባለች
በሌሊት ሲውሉ፣

ምንም ባለበት ዓለም፣
ምንም ነገር የለም፣
ረስቶናል ባሉት ስንቱ አመነው
በድንግዝግዝ ቀለም
ከሰማይ የራቀ ስንት ምፅአት ተገዝቶስ የለም፣

ደሞም ዳሩን ክደው
የአጥናፍ ሰማይ ዝርጉ፣
ተላላ መሆኑ
ከሰው አይቆጠር  የእንባ አዝናቢ ዝንጉ፣

ተስፍን በሙቀጫ ሰማይ ጋር ማራቁ፣
ያልታደሉትማ እግዜሩን አታለው
መንበሩን ሰረቁ፣
በመጥለቅ ሰማይ ስር በመንጠቅ ጮለቁ፣

ሰው እና ተስፍውን፣
እምነት እና እምባውን፥
ከደመና ልኬት፣
የእንባ ጤዛ ተኖ
ከሰማይ ርቋል ሀገር እና ስኬት፣

ከኮከብ ማገዙ የሰውነት ገላም፣
ከሰማይ ተረግጧል
ምድር ባሉት እግር ፍቅር እና ሰላም፣
እናም...

እንጠቅ እንዲሉ በመውረድ ወደላይ ፣
ዝቅ አንበል አሉት
ከታች ለሚወድቁ ለማይሰማ ሰማይ፣
ለምድርም ታች አለው
በደመነ ለታ የሞት ቀኑ ሲሳይ፣

ቻው እማይ...


___
ግዕዝ ሙላት

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19