Get Mystery Box with random crypto!

#ከጎንደር_እስከ_መኧለ #ምዕራፍ_1 #ክፍል_03 (ግብዣ) የታንጉት ግሮሰሪ ከቀን ወደ ቀን ገብ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

#ከጎንደር_እስከ_መኧለ

#ምዕራፍ_1
#ክፍል_03 (ግብዣ)

የታንጉት ግሮሰሪ ከቀን ወደ ቀን ገብያው እየቀዘቀዘ መጣ....እንደዛ ቤቷን የሚያሞቅላት ተተራራቢ ጎልማሶች ዛሬ በግሮሰሪው የሉም...ደራሲ አብዮትም ከግሮሰሪው ከራቀ ብዙ አመታት አልፈውታል...ተከራይቶባት ከነበረችው ትንሽዬ ቤቱን ከለቀቀ ቆይቷል።

ነገሩ ሁሉ አዲስ ነገር ሆኗል...የአዘዞ ድማዛ ድልድይ ከድሮው በይበልጥ አምሮበታል...ከድልድዩ ስር የሚፈሰው ውሃ በተለያዩ አዕዋፋት ተከቧል...ፀሃዯ እጅግ ደስ ትላለች...ድልድዩን በግራና በቀኝ ያጀቡት ረዣዥም ዛፎች አካባቢውን ይበልጥ ሳቢ አድርታል...ከታንጉት ግሮሰሪ ዝቅ ብሎ የተገነባው ትልቅ የገበያ አዳራሽ በሰው ተጥለቅልቋል።

የጎንደር ከተማ በደራሲ አብዮት መፅሃፍ ገበያዋ ሞልቷል...ባሏት ረዣዥም ፎቆች ላይ የደራሲን አብዮትን ምስል የያዘ ባነር ሰቅላለች...ከባነሩ ስርም "ነገር ተቀይሯል...ይቀየራልም" የሚል ጥቅስ ተፅፏል።

ደራሲ አብዮት ያለበትን አድራሻ ማንም የሚያውቅ የለም ከብዙ በአንድ ጊዜ ትላልቅ መድረኮች ላይ ይሳተፋል...በሚሳተፍበትም ወቅት ብዙ ነገሮችን ይናገራል...ብዙውን ጊዜ መድረክ ላይ ግጥም ሊያነብ ወይም ደሞ ከልብ ወለዱ ላይ ቀንጭቦ ሊያነብ አይወጣም...ልክ የድምፅ ማጉያውን እንደጨበጠ የሚናገራቸው ነገሮች ከአለም ውጭ ያሉ ነው ሚመስሉት...ከበፊቱ ይልቅ አሁን ላይ ዝነኛ እና ታዋቂ ሆኗል..ተወዳጅም ጭምር....ማንም የሚዲያ ሰራተኛ ለጥያቄ ቢጋብዙት መልሱ "አይሆንም" ነው። ብዙ ጊዜ በስልክም ቃለ መጠየቅ ሊያደርጉለት የፈለጉ ጋዜጠኞችን መልስ አይሰጣቸውም....ምክንያቱ ደግሞ "እንደዚ ዝነኛ እና ታዋቂ ከመሆኔ በፊት የምናገረውን ቃል አንድም ያላዳመጠኝ ማህበረሰብ አሁን ስሜ ሲገን ለምን እኔን ፈለገ" ይላል።

"አለምን ማስቆም አንችልም ወይንም ደሞ እሷ ጋር እግር በግር መከተልም ይከብዳል...ስለዚህ ያለን አማራጭ አያስመሰልን መግፋት ነው። ከአለም ጋር አብረህ መሄድ ሳይሆን እየሄድክ ማስመሰል ነው ያለብህ...አለም በወደቀች ቁጥር መንገድህን አስተውል።" ደራሲ አብዮት በአንድ ወቅት ከታንጉት ግሮሰሪ እየጠጣ የተናገረው ነበር....በአሁን ሰዓት ከአመታት በፊት አብረውት ለነበሩት ሰዎች የሚነግራቸውን ነገር በ ማህበራዊ ገፅ ያስተላልፉታል...."አቢ...ለምንድነው ምትጠጣው" ሲባል "ከባህር የገባን ሰው ባህር ውስጥ ገብተህ እንጂ ዳር ቆመህ በእንጨት አትስበውም...ብቃት ካለህ የዛን ሰው ህይወት ከባህሩ ውስጥ ታወጣታለህ ደካማ ከሆንክ ግን አብረኸው ትሰጥማለህ....ያወራሁህ ስለመጠጥ አይደለም ስለ እኛ ነው እንጂ"።
"ብዙውን ጊዜ ፍቅረኛ ለመያዝ መጣደፍ  ልክ እሳትን በእጅ እንደመጨበጥ መጓጓት ነው...በእሳት ልጫወትም እንደማለት ነው... ምክንያቱም ፍቅር ምን እንደሆነ ስላልተረዳነው... ዘመናዊ ለመባል ብዙ ሴት ጋር ምታወራ ከሆነ መንገድህን አስተካክል ምክንያቱም ከዘመናዊነት አልፈህ ነፃ የ ዋይፋይ ኔትወርክ ስለሆንክ...ሁሉም በፈለጉህ ሰዓት ከራሳቸው ጋር ያገናኙሃል...መንገድህን አስተውል".....ደራሲ አብዮት ከአመታት በፊት ከሚጠጣባት ታንጉት ግሮሰሪ ውስጥ ከሚያውቁት ሰዎች ሁሉም ስለሱ ሙሉ ነገር አያውቁም...አንድ የሚያውቁት ነገር ደራሲ እና ገጣሚ እንደሆነ ብቻ ነው።

ደራሲ አብዮት ወጋየሁ የፃፈው ልብወለድ በ ሬድዮ መተረክ ጀመረ...." ከምሽቱ 3 ሰዓት ለአድማጮቻችን የሚተላለፈው የትረካ ሰዓታችን እነሆ ጀምረናል የዛሬው ትረካ ** ከሚለው የረዥም አጭር ልብወለድ መርጠን ለናንተ እናቀርባለን ከማስታወቂያዎች በኋላ እንመለሳለን"

" #ትውልደ_መኧለ ....ደራሲ አብዮት ወጋየሁ.....ተራኪዎች ኪሩቤል መስፍን እና ፍሬህይዎት ሺፈረው"

ይቀጥላል...

ዮኒ
    ኣታን @yonatoz

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19