Get Mystery Box with random crypto!

» ብላ አጠገቤ ደርሳ የለበስኩትን ሹራብ ግልብ ስታደርገው ግራ ገባኝ እና መነጨቅኳት። የቆሙትን ጠ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

» ብላ አጠገቤ ደርሳ የለበስኩትን ሹራብ ግልብ ስታደርገው ግራ ገባኝ እና መነጨቅኳት። የቆሙትን ጠባቂዎች (መሰሉኝ) ፊታቸውን እንዲያዞሩ ምልክት ስትሰጣቸው ሶፋው ላይ ያለው ሰውዬ እራቁቴን የማየት መብት እንዳለው ሁሉ ዝም አለችው። ከንግግሯ ምናልባት የምናወራውን የምቀዳበት ነገር ሰውነቴ ላይ ደብቄ እንደሆነ እያጣራች መሆኑ ገባኝ። በፓንት እና በጡት ማስያዣ ስቀር አይኑን ከሰውነቴ ላይ ለመንቀል ምንም ሀሳብ የሌለውን ሰውዬ እያየሁ መዋረድ አንገበገበኝ። ሴትየዋ ጡቴ ስር ገብታ ስታንቀረቅበኝ ጡቶቼን የምትመዝናቸው እንጂ የሆነ መቅጃ ያለችውን ነገር እየፈለገች አይመስልም። ጥርሴን ነክሼ ዋጥኩት። ሆነ ብላ የምታደርግ ነው የሚመስለው። ጣቷ የእንትኔን ጫፍ እስኪነካው ድረስ እጇን ፓንቴ ውስጥ ስትሰድ እስኪያማት ድረስ የእጇን አልቦ ማሰሪያ ጨመደድኩት።

«ok ok » ብላ እጇን አወጣች። የያዝኳትን ስለቀው ቦታው ደም መስሏል። ፊቷ ላይ ያስታውቃል። ከመፈተሿ በላይ እኔን ማዋረዷ ተመችቷታል። እንድለብሰው ልብሴን ከመሬት አንስታ ወረወረችልኝ። ከሰውየው ጋር ተያይተው ያልገባኝን መልዕክት ተለዋወጡ። ይዤው የነበረውን ቦርሳ አንስታ አመሳቅላ በረበረችው።

«አላመንከኝም እንጄ ነግሬህ ነበር,» አለችው። ሰውየው ባለችው ነገር ሙሉ በሙሉ ያመነ አይመስልም።

«እሺ ሜላት!! የታሉ ቪዲዮዎቼ?» አለ

«ወንድሜን በአይኔ ሳላየው ምንም ነገር አልነግርህም!!» አልኩት ለመኮሳተር እና ያልፈራ ለመምሰል እየሞከርኩ።

«ሜላት ይሄ ኔትፍሊክስ ላይ ተጥደሽ ስታዪ የምትውዪው የሆሊውድ ፊልም አይደለም። አጉል ጀግና ጀግና አትጫወቺ!! የትም አትደርሺም!!» አለ ልጥጥ ብሎ እንደተቀመጠ። አልመለስኩለትም።

«እየሰማሽኝ አይደለም? ዛሬ የምጫወትበትን ጠጠር የምመርጠው እኔ ነኝ። ያልኩሽን ነው የምታደርጊው።» ብሎ አምባረቀ።

«ወንድሜን ካላየሁ ምንም የማደርገው ነገር የለም አልኩ እኮ!!» ብዬ ለመጮህ ሞከርኩ።
ለቆመው አጭሩ ጠባቂ ምልክት ነገር ሰጠው። የታመቀ ትንፋሼን በረዥሙ ለቀቅኩት። ኪዳን ሲገባ ምንም የተጎዳ ነገር ያለው አይመስልም። ሲያየኝ ፊቱ ላይ ከቃላት በላይ የሆነ ስቃይ አየሁበት።

«I am so sorry» አለኝ ገና ስንተያየኝ። አልከለከሉኝም! ሄጄ አቀፍኩት። አጥብቆ አቀፈኝ። «ይቅርታ ሜል!»

«መልሰው!!» ብሎ ጮኸ ሰውየው። አብሬው እንድቆይ ብለምንም ሊሰማኝ እንኳን ግድ አላለውም። ምንድነበር ያሰብኩት? 'ናፍቆትሽ እስኪወጣልሽ እንጠብቅሻለን ከወንድምሽ ጋር ትንሽ ተወያዩ' እንዲሉኝ ነበር? የምርም እንዴት ያለ የቂል እቅድ ነው ያወጣሁት? ኪዳን ተመልሶ ሲሄድ የተሸነፍኩ መስዬ ላለመታየት ሞከርኩ። ሰውየው ወደእኔ አፈጠጠ።

«ሁሉንም ኮፒ እንዳመጣልህ አይደል ፍላጎትህ? በሰጠኸኝ አጭር ጊዜ ላመጣልህ አልችልም!! ተጨማሪ 24 ሰዓት ስጠኝ እና የምትፈልገውን በሙሉ እሰጥሃለሁ።» ስለው ያሳቃቸው ጉዳይ አልገባኝም ሁለቱም ከጣሪያ በላይ ሳቁ።

«ብዬህ ነበርኮ! በል ብሬን ወዲህ በል!» አለችው ሰትየዋ እጇን እየዘረጋች።

«እያወቅሽኝ ካላረጋገጥኩ መች አምናለሁ?» መለሰላት። እየሆነ ያለው ሙሉው ባይገባኝም እያላገጡብኝ እንደሆነ ገብቶኛል። ከኪሱ የሆኑ ብሮች ኖት አውጥቶ አቀበላት።

«ባንቺ ቤት አቃቂለሽኝ ሞተሻል!! ካንቺ ውጪ ማንም መረጃዎችሽን የት እንደምታስቀምጪ እንደማያውቅ ገምቻለሁ። እመቤትን ነበር የጠረጠርኩት እንደገባኝ እሷም የረዳችሽ ነገር የለም። አንቺም የት እንዳስቀመጥሽ እንዳታስታውሺ ትውስታሽ ላይመለስ ከድቶሻል። ንገሪኝ እስኪ ምን ልሁን ብዬ 24 ሰዓት ልጠብቅሽ?» ሲለኝ የበለጠ ጅልነት ተሰማኝ።

ባለፈው ከደበደቡኝ ጎረምሶች የተሻለ እነዚህ ሰዎች መረጃ ከፈለጉ በቀላሉ ማግኘት አይችሉም ብዬ እንዴት አሰብኩ? ምኗ ቂል ነበርኩ? አሁን ይገድሉኛል? እሺ ኪዳንንስ? ምንድነው ያደረግኩት?

በሩ ተከፍቶ የቅድሟ ሴት በሩ ላይ ላለው ጠባቂ የሆነ ነገር አንሾካሽኳ ወጣች። ጠባቂውም የሆነ ነገር ለሰውየው አንሾካሾከ። ሰውየው በጣም የተገረመ መሰለ።

«ያንቺው ጉድ ነው!» አላት ወደሴትየዋ እያየ። ሴትየዋ ግራ የተጋባች መሰለች። በጣም በመገረም ወደበሩ እያየች።
«ምን ልሁን ነው የሚለው አስገቡት እስኪ!»

ዓይኔ የሳተው ነገር ቢኖር ነው። ጆሮዬም እንደዛው? <የሷው ጉድ> ነው ያለው ወይስ <የአንቺው ጉድ> ነው ያለው? የእኔው ጉድ ጎንጥማ የሷው ጉድ ሊሆን አይችልም። ወይም ሌላ ጎንጥ ይሆናል እንጂ የእኔው ጎንጥማ አይሆንም!! በሩን አልፎ ሲገባ ቤቱ ነው የሚመስለው!! ልክ የእናት አባቱ ቤት እራት ሊበላ እንደመጣ ነገር ዘና ብሎ ከሶፋው ተሻግሮ ያለ ወንበር ሳብ አድርጎ ተቀመጠ።

እስከአሁን የነበረው ምኑም ያየኋቸውን ፊልሞች አይመስልም ነበር። ይሄ ግን ፊልም እንጂ እውን አይመስልም።

«ምን ትሰራለህ?» ብላ ሴትየዋ ጮኸች።

«ስራዬን ነዋ!!» አለ እንደማላገጥ ብሎ

ሆድቃዎቼ ቦታ የተቀያየሩ ነገር መሰለኝ። ሆዴ ውስጥ ተለዋወሰብኝ።

.......... ይቀጥላል........

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19