Get Mystery Box with random crypto!

አወይ የሷ ነገር አወይ የሷ ስቅለት፤ በደል ሳይገኝባት ምግባር ሳይጎልባት፤ ተገርፋ በጥፊ ተመታ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

አወይ የሷ ነገር አወይ የሷ ስቅለት፤

በደል ሳይገኝባት ምግባር ሳይጎልባት፤

ተገርፋ በጥፊ ተመታ ላታሳልፍበት፤

መስቀሏ ላይነሳ ደንድኖ ሲሳናት፤

ቀራንዮን ስትመኝ ልታርፍ በስቅላት፤

ከወዴት ትሄዳለች? ጵላጦስ ሄሮደስ ሳይሆንባት ተርት።


በር ያለበት ሁሉ ቤተ መንግስት ሆኖ፤

ሄሮደስ ጵላጦስ በየበሩ ሞልቶ፤

እዝኛዉን ስትጨር ወደዝያኛው ተብሎ፣

ማለቂያ ያለው ዕለተ አርብ ጠፍቶ፤

ወዴት ትመጣለች ? ፍርድ ቤቱ በዝቶ።



አይዞሽ ትደሪሽያለሽ ታርፍያለሽ ተሰቅለሽ፤

ዳግም ላትቀምሽ የችንካሩን ጣእም ትቀምሽያለሽ ወደሽ፤

ቀራኒዮን በእምባ ጎልጎታን በዋይታ ትደርሽያለሽ መተሽ፤

ምጥሽ የከበደሽ ኢትዮጵያ እናቴ ይዞ የሚመጣ ያን ትንሳኤሽ ፤

ስቅለትሽ ይቅረብሽ እላለሁኝ እኔ።
(ስብሐት ወገን ከወላይታ)

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19