Get Mystery Box with random crypto!

            ልወዳትነውመሰል .     ''''''''''''''''''''''''' ልወዳት ነው | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

     
      ልወዳትነውመሰል
.     """""""""""""""""""""""""
ልወዳት ነው መሰል ልቤ ጠረጠረ
ቀልቤ እኔን ጥሎ እሷ ጋር በረረ
አያት እንዳልነበር እንደ ንፁህ እህቴ
ታዲያ ምነው ዛሬ እንቅልፍ ማጣቴ
አይኗን ካላየው ድብርት ውስጥ መግባቴ
.
ልወዳት ነው መሰል ትናፍቀኛለች
በደቂቂቃ ሲኮንድ ትዝ ትለኛለች
ከሌላ ጋር ሳያት በቅናት ማበዴ
አፈቀርኳት መሰል ወቸው! በል ዘመዴ
.
ልነግራት ስፈልግ የልቤን አውጥቼ
ፍቅሬ እንድትሆን በፅኑ ጓጉቼ
ግን ደግሞ እንደገና እጠራጠራለሁ
እህትነትሽን እንዳላጣ ሰጋሁ…
.
ልወዳት ነው መሰል ልቤ ጠረጠረ
በቃ! እነግራታለሁ በኔ አልተጀመረ።

        ተፃፈ በ አቤል

   
ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19