Get Mystery Box with random crypto!

. ግን ለምን? ከቤተስኪያን ግቢ ፊቷን ተከናንባ ፀጥ ካለው ግቢ አጎንብሳ ገብታ ከበሩ ስ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

. ግን ለምን?

ከቤተስኪያን ግቢ ፊቷን ተከናንባ
ፀጥ ካለው ግቢ አጎንብሳ ገብታ
ከበሩ ስር ስትደርስ ዝቅ ብላ ተደፍታ
'ምስጋና ለአምላኬ ሁሉን ለምታቀው
የታመመ ባሌን ከህመም ላዳንከው
የወለድኩት ልጄን ብሩክ ላደረከው
አመሠግናለሁ
ነገም አለኝታህን እጠባበቃለሁ

ደህና አርግልኝ ባሌን ሰላም ወጥቶ ይግባ
አሳድገው ልጄን ከፍ ይበል ያባባ
(ጠብቃት ሀገሬን ይከበር ድንበሯ)
የታረዘን አስብ ሸክፍ የደሀ እንባ
ይፅደቅ የሞተ ሰው ይዳን የታመመ
ይርካ ውሀ የጠማው ይጥገብ የተራበ'
ብላ ትነሳለች
ከብብቷ ጉያ
ካለች ጥቁር ቦርሳ
...ሳንቲም ታወጣለች
አንዷን ፍሬ መዛ ሙዳይ ታገባለች
ፀጥ ካለው ግቢ አፀድ ከበዛበት
እልፍአእላፍ ሰላምን ከሚጎነጩበት
ወጥታ ትሄዳለች
ገንዘብ ስጠች አትል ወይ ወርቅ አልጠየቀች
ማጌጥ አላማራት ውበት አለመነች
::::::::::::::::::::::::::://:::::::::::::::::::::::::::
አጉል ቀኑ ቀድሞት ከዘመን ተኳርፎ
የዛች የምስኪን ባል ከዕድሜው ላይ ፎርፎ
ፀጥታ በራቀው ጩኸት በበዛበት
ዝምታ ቅጥ ባጣ ሁካታ ባለበት
በመጠጥ ዱቅዱቅታ በዘፈን አታሞ
በሽቶ በጠረን በእልፍ ሴት ተከቦ
ከጨለማው መሀል በታየች ብልጭታ
ከሰይጣን ቁጭ ብሎ ትዝ ቢለው ጌታ
ይሄንን ለመነ...
'ያቺ አሮጊት ሚስቴን ድፋልኝ ልቅበራት
ያገሩን ቆንጆ ሴት እንዳሻኝ ልግመጣት'
የምን ጥያቄ ነው? ምን ይሉት ልመና
ምን አይነት ፍላጎት?ምን አይነት ፅሞና?
ሰላም እንዲያረገው ደስ ብሏት ሳትጨርስ
ስለት አስገብታ
አልፈልግም ትሂድ ግደላት ውሰዳት
የሚሉት ውትወታ?
::::::::::::::::::::::::::://:::::::::::::::::::::::::
የዛች የምስኪን ሴት የአብራኳ ክፋይ
የአምላክ ማመስገኛ የአካሏ ምሳይ
ቃል በደንብ ሳይፈታ ገና ባ'ፍላነቱ
ያ ችኩል ያ ፈጣን ያ ልጇ ወጣቱ
ከሀያ አመት በላይ አብራው ለኖረችው
አዝላ ተንከባክባ ጡቷን ላጠባችው
አንዲት መስመር ሳይፅፍ...

በአንድ ቀን እይታ ድንገት ለከነፈ
5 ገፅ በሙሉ አንድ ደብዳቤ ፃፈ
'እኔ ያንቺ ብቻ ነኝ' ብሎ ለፈለፈ
ሌላውን ረስቶ ያቺን ልጅ አመነ
'እሷን ብቻ ስጠኝ' እያለ ለመነ
:::::::::::::::::::::::::://::::::::::::::::::::::::::
አይ የዚች አለም ጉድ - ግራ አይሉት ወይም ቀኝ
ከላይ ቢሉት የለ - ከታች ቢሉ አይገኝ
አሁን ያቺ ጎጆ ያቺ ሶስት ጉልቻ
በማን ነው የቆመች በማንስ ትክሻ?

የማን ነው ትክክል የትኛው ነው ስህተት?
የቱ ነው እውነቱ የማንስ ነው ሀሰት?
ማን ተጠራጠረ ማንስ ነው ባለእምነት?

እሷ ስለልጇ ለባሏ ላ'ገሯ
ታርዞ ላየችው ላለፈ በበሯ
ለሁሉ ስትለምን
እሷን ማን ዞሮ አየ - ግን ለምን ግን ለምን?


በአቤኒ የተፃፈ


ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19