Get Mystery Box with random crypto!

አቻ የለሽ ውበት ጠፈር በከዋክብት ደምቆ፣ በጨረቃ ብርሃን ተጠምቆ፣ እልፍ ውበታትን በላዩ ቢደፋም | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

አቻ የለሽ ውበት

ጠፈር በከዋክብት ደምቆ፣
በጨረቃ ብርሃን ተጠምቆ፣
እልፍ ውበታትን በላዩ ቢደፋም፣
ለኔ አንቺን አያኽልም፤አይስተካከልም።

ሔለን ሺ ጊዜ ተወልዳ_
ሺህ ጊዜ ብታምርም
ሺህ ጦረኛ ቢሞት_እልፍ ቢናገርም
"ሔለን የግሪኳ፣ሔለን የጥንቲቷ
ስንቱንጎበዝጀግናማረከችበውበቷ"
ብሎቢዘምርም፤
ለኔ እንዳንቺ አታምርም፤አትስተካከልም።

ቬነስ ከመንበሯ ወርዳ፣
የአዳም ዘርን ሁሉ በፍቅሯ አሳብዳ፣
ፍጥረት ለውበቷ ሰግዶ፤
ለዉበቷ ማልዶ፤
ቆንጆናት ቢላትም
ለኔ እንዳንቺ አታምርም፤አትስተካከልም።

≈ተፃፈ በኤሮስ

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19