Get Mystery Box with random crypto!

ሀሊማ ክፍል 1 ፡ 'ህይወት አንዳንዴ እኛ እንደ ምንፈልገው ሳይሆን እሷ እንደ መረጠ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ሀሊማ


ክፍል 1


"ህይወት አንዳንዴ እኛ እንደ ምንፈልገው ሳይሆን እሷ እንደ መረጠችው ነው የምንኖረው"
.
ዛሬም እንደ ወትሮዋ ከእኩዮቿ ጋር ለመጫወት ከ ቤት ወጥታ ወደ ጓደኞቿ ጋር ሄደች፡፡ ሀሊማ በጣም ተጫዋች ደስተኛ እና ሁሉም ሰው የሚወዳት አይነት ልጅ ናት የተወሰነ ሰአት
ከተጫወተች ወዲህ እረሀብ ቢጤ ተሰማት ያው የልጅ ነገር እረሀቡን ለማስታገስ ያህል ብቻ ነው እነደነገሩ ምግቡን ቀመስ ቀመስ የሚያደርጉት፡፡ ከዛ ወደ ጨዋታቸው ይመለሳሉ ፡፡ ሰአቱ ከ ጠዋቱ 5፡30 ይላል ሀሊማ ጓደኞቿን ተሰናብታ ወደ ቤቷ ሄደች ፡፡ ነገር ግን እቤቷ ስትደርስ ያልጠበቀችውን ነገር ያጋጥማታል ያ ክስተት ህይወቷ አንዲከብድ ያ ያሰለፈችው ጨዋታ እንዳይደገም የደረገውን ደስታዋ ሁሉ ጠፍቶ ቀሪ ጊዜዋን በ ሀዘን እንድታሳልፍ
ያደረገ ክስተት ነው ሀሊማ በራፍ ላይ ስተደርስ ያልጠበቀችው ነገር ያጋጥማታል ያለ ወትሮ የግቢቸው በር ተከፍቶ ታገኘዋለች ትንሽ ግራ ገባት ምን አልባት ኡሚ እደከፈተችው ረስታው ይሆናል ብላ አሰበች በሩን ድምፅ ሳታሰማ ቀስ አድርጋ ዘጋችው ፡፡ሌላ ግዜ
እንደምታደርገው እናቷን ጋር ሰትደርስ በቀስታ ኮቴ ሳተሰማ ትሄድና ታስደነግጣት ነበር ዛሬም እንደ ወትሮዋ እናቷን ለማስደንገጥ እናቷን ሁሌ ወደ ምታገኝበት ቦታ ኩሽና ሄደች ግን
እንደጠበቀችው አልሆነም እናቷን ኩሽናው ውስጥ ልታገኛት አልቻለችም ምን አልባት ሳሎን ትሆናለች ብላ ወደ ሳሎን ቤት በተመሳሳይ መልኩ እየተራመደች ሄደች ግን እዛም ቢሆን
ተመሳሳይ ነገር ነው ያጋጠማት ሀሊማ እናቷ ያለወትሮዋ ሁሌ ከምታገኛት ቦታ በማጣቷ ትንሽ ግራ ተጋብታ ቁጭ ብላ መጠበቅ ጀመረች ኡሚ ...ኡሚ... ብላ ልትጠራት አስባ ግን ድንገት አንድ
ሀሳብ መጣላተ መኝታ ቤት ለምን አላያትም የሚል አሁንም እዛም ቢሆን ካገኘቻት ከሃላዋ ሆና ለማስደንገጥ እንዲያመቻት ቀስ አያለች ወደ መኝታ ቤቱ አመራች ነገር ግን የሆን ድምጽ ሰማች የ
እናቷ ድምጽ አይደለም ማን ይሆናል ያለው እያለች እየፈራች ወደ ክፍሉ ተጠጋች በሩ አልጠበቀም ነበርና ቀስ ብላ ጠጋ አደረገችው የ አባቷ ድመጽ ሰማች በዚህ ሰአት እቤት ምን ይሰራል ብላ አሰበች ጠዋት ቁርስ ከበሉ በኃላ ስራ እንደሄደ አስታወሰች ታዲያ እንዴት መጣ ብላ እያሰበች በሩን ከመጀመሪያው ትንሽ ጠጋ አድርጋ አንገቷን ወደ ውስጥ አስገባች ግን ምንም ያልጠበቀችው ነገር ነበረ የተመለከተችው ሁለት አንድ አመት ያልሆናቸው ታናናሽ መንታ እህትና ወንድሟ አልጋው ላይ እን ተኙ ናቸው፡፡ የሀሊማ እናት ግን
:
:
አልጋው ግርጌ ጋር በጀርባዋ ተንጋላ ወድቃለች ከ አንገቷ አካባቢ ደም እየፈሰሰ ነው፡፡ አባቷ ደንግጦ ባለበት ደርቆ ቆሞዋል ከአልጋው ጎን ሰሚራ የሆነ ብረት የሚመስል ነገር ይዛ ቆማለች
ሰሚራ ማለት ጓረቤታችን እና የ እናቴ የቅርብ ጓደኛ ነች እኔ ሳልወለድ ጀምረው ጓደኛ ናቸው አሁን እኔ ሰባት አመቴ ነው እነሱ ከዛም በፊት ጀምሮ ጓደኛ ናቸው ነገር ግን ዛሬ ያየሁትን ነገር ማመን አልቻልኩም ብረቱን ለምንድነው የያዘችው ምን ልታደርግበት ነው ብዬ አሰብኩ...... አባቴ ራሱን ከመሳት በማይተናነስ መልኩ ነበር ደንግጦ
የቆመው፡፡ አባቴ ትንሽ ወደ እራሱ እንደመመለስ ሲል ወደ እናቴ ተጠግቶ ለማንሳት ሲሞክር በድንገት ሰሚራ ፊቷን አጨማዳ
.
"ምን ለማድረግ እየሞከርክ ነው" ብላ ጮኧችበት .......ወደ ሀኪም ቤት ልወስዳት ነው አላት እየተርበተበተ
በምላሹም ሰሚራ ......."ከዛስ ባክህ ምን ሆና ነው ሲሉህ ምን ልትላቸው ነወ እኔ እና የባለቤቴ ጓደኛ በጣም ስለተዋደድን እሷን ደግሞ መፍታት ስለማልችል እኔ እና ሰሚራ ተመካክረን
ልንገድላት አስበን ሰሚራ በብረት ጭንቅላቷን መታት ነው ብለህ
ልትነግራቸው ነው " ብላ አፈጠጠችበት ይሄን ስሰማ በዛ በጨቅላ አቅሜ መሸከም ከምችለው በላይ ነበር ሰሚራ ብረቱን ለምን እንደያዘችው ያኔ ነበር የገባኝ መቋቋም አቃተኝ የሰማሁትን
ማመን አልቻልኩም አንድ ሰው ከሞተ ድጋሚ ከሰዎች ጋር መገናኘት እንደማይችል ነበር እናቴ የነገረችኝ ታድያ እናቴንም ድጋሚ ላገኛት አልችልም ማለት ነው .......ስለ ሞት እንኳ በቅጡ
አላውቅም ነበር አይሆንም አባቴ እንዲህ አያደርግም አባቴ እናቴን በጣም ነወ የሚወዳት እያለኩ ከ እራሴ ጋር አወራለሁ፡፡ አባቴም መናገር ጀመረ ይበልጥ ተጠግቼ ማዳመጥ ጀመርኩ እሱ ይሄን እንደማያደርግ እንዲያረጋግጥልኝ በማሰብ ግን.....

.......... ይቀጥላል........

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19