Get Mystery Box with random crypto!

​​ሀሊማ ክፍል 2 ፡ ፡......አባቴ መናገር ጀመረ ግን እኔ እንደጠበቁት ሳያሆን | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

​​ሀሊማ


ክፍል 2


፡......አባቴ መናገር ጀመረ ግን እኔ እንደጠበቁት ሳያሆን የበለጠ
እንደገደላት የሚያረጋግጥ ነገር ነበር የተናገረው.....ሰሙ ልክ ነሽ አለ ግን..... ሲል እንዳትጨርሰው......ምንም ግን የሚባል ነገር የለም ባይሆን ሬሳዋን ምን
እንደምናደርገው እናስብ አለችው....እሺ ልጆቼስ አላት ለእነሱ እኔ አለሁ ደግሞ ተነጋገርንበት
አይደል አለችው..........አባቴ በጣም በጨነቀው ድምፅ እሺ ለ ሀሊማስ እናቴስ
ካለችኝ ምን ልላት ነው........የሆነ ምክንያት እንነግራታለን ቤተሰቦቿን ለመጠየቅ ክፍለ
ሀገር እንደ ሄደች ወይም ሌላ ምክንያት እንነግራታለን አለችው.....ሌላ አማራጭ ስለሌለው እሺ አላት ይህንን ሀሊማ ስትሰማ
ምድር የተደፋባት የህል ነበር የተሰማት በሩን ከፍታ ወደ ወስጥ
ገብታ የእናቷን ሬሳ ለመንካት ድጋሚ የማላገኛት ከሆነ ልሳማት
ብላ አስባ በሩን ጠጋ ለማድረግ ስትሞክር ሰሚራ እጅ ላይ
ያለውን ብረት ተመለከተችው እናቷን ብረቱ መትታት
እንደገደለቻት ስትናገር ሰምታለች የእናቷ እጣ ለ እሷም
እንዳይደርሳት ፈራች ልትከፍተው የነበረውን በር መልሳ ተወችው
የእናቷን ሬሳ ለመደበቅ ሲዋከቡ አየቻቸው ሞት ማለት ምን
እንደሆነ በማታውቅበተ እድሜ ላይ ሆና በንጹህ አእምሮዋ የ
እናቷን አሰቃቂ ሞት የ አባቷ ጭካኔ አየች አባቷ ይህ ሁሉ ሲሆን
ሀሊማ እንደማታውቅ ነው ያሰበው ከመኝታ ቤቱ ለመውጣት
ሲሞክሩ ሀሊማ በሞተ አቅሟ እተንቀጠቀጠች ቤቱ ለቃ ወጣች
በጣም ስለደነገጠች ሰውነቷ ደርቆዋል ወዴት እንደምትሄድ
አታውቅም እንዲሁ እግሯ ወደ መራት አቅጣጫ መሄድ ጀመረች
ረጅም መንገድ ከሄደች በሃላ ወዴት እየሄደች እንደሆነ ግራ
ገብቷት አንድ ጥግ ላይ ተቀምጣለች............
.....እንደ አጋጣሚ ሆኖ ሀሊማ በተቀመጠችበት መንገድ
የሀሊማ
የእናቷ የቅርብ ዘመድ የሆነችው ፋጡማ በዚያ መንገድ ስታልፍ
ሀሊማን በ አትኩሮት ተመለከተቻት ሀሊማ ግን ቀድማ ፉጡማን
አይታታለች ግን ማን እንደሆነች ማገናዘብ አልቻለችም
ፉጡማም ግራ በተጋባ ሁኔታ አየቻት ፊቷ አዲስ አልሆነባትም
በደንብ ለማየት ሞከረች ግን የሀሊማ ሂጃብ ስለተዝረከረከ
ከፊል ፊቷን ሸፍኗታል ማን ትሆን እያለች ማሰብ ጀመረች እንደዚ
ትንሽ ልጅ የት ነው የማውቀው ብላ ትንሽ እንደማሰብ ካለች
በኃላ የ አክስቷ ልጅ የሆነችው ዘይነባ የሷ ልጅ ሀሊማ ትሁን ብላ
አሰበች ሀሊማ ብትሆን አይታኝ ዝም አትለኝም እንኳን እንዲ
አይታኝ በ ስልክ እራሱ እንዴት እንደምትሆን እያለች ብቻዋን
እያወራች ደግሞ እዚህ ድረስ ምን ልትሰራ መጣች በዛ ላይ
ብቻዋን አይ እሷ አይደለችም ብላ አልፋት ሄደች.......

.......... ይቀጥላል........

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19