Get Mystery Box with random crypto!

የካድኩት ልጅ አለኝ ወልጄ 'ማላቀው አሱም የማያቀኝ። ግሩም ድንቅ ፍጡር ከሱ በላይ ላሳር። አይኖ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

የካድኩት ልጅ አለኝ
ወልጄ 'ማላቀው አሱም የማያቀኝ።

ግሩም ድንቅ ፍጡር
ከሱ በላይ ላሳር።
አይኖቹ ከዋክብት ጠይም አሳ
መሳይ
እኔን እናቱን ሲሆን አይኑ ዞሮ 'ማያይ

ምጡቅ አንጎል አለው
አለም ያደነቀው
ግንሳ.... ብልሀት ጎደለው።
አንጀቱ እንስፍስፍ
ማየት የማይችል ግፍ።
ግንሳ ለናቱ....
አይራራ አንደበቱ።

እናትህ ትቃጠል እናትህ እንዲ
ትሁን
እናትህ..... እናትህ.....የስድብ
ውርጂብኝ።

የካድኩት ልጅ አለኝ
እሱም የማያቀኝ
ስድብ የሚያረገኝ
አስር ጣት እያለው...
ሁለቱን ሦስቱን ካልቆረጥኩ
የሚለኝ።


ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19