Get Mystery Box with random crypto!

ደግሞ የነገን ማን ያውቃል! (ታደሰ ደምሴ) አንዳንዴም... ጀምበሯ ቀዝቀዝ ስትል ሰማዩ ደመንመን | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ደግሞ የነገን ማን ያውቃል!
(ታደሰ ደምሴ)

አንዳንዴም...
ጀምበሯ ቀዝቀዝ ስትል
ሰማዩ ደመንመን ሲል
አየሩ ሲቀዘቅዘኝ
ከላይ በረከት ሊወርድ፣
ሊዘንብ እየመሰለኝ

አንገቴን አንጋጥጥና፣ሸቅቤ አማትራለሁ
ግና ደመና ነው ያልሁት፣ጉም ሆኖ ሲተን አያለሁ
ይሔው ...
ካምና እስከ ዛሬ ፣በውሃ ጥም እንደተቃጠልሁ
የምሻው ቀኔ ተባርኮ፣የነፍሴን ቀለብ አልተቸርሁ
የጸጋ ሲሳይ ዘንቦልኝ፣ጠጥቼ ጥሜን አልቆረጥሁ
እንዲሁ ...
"ማን ያውቃል የነገን" ብየ፣እንዳማኝ እየተጽናናሁ
ብሶቴን በተስፋ አርክሼ፣ሁሉንም እታገሳለሁ!
ቻል!!!


ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19