Get Mystery Box with random crypto!

የሞት ንፋስ በምድሪቱ ባለነበረ አይነት ነፈሰ ። ደቂቅ ሊቁን እያፈሰ ፤ ያቀፉትን እየቀማ ቀሪዎቹን | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

የሞት ንፋስ በምድሪቱ ባለነበረ አይነት ነፈሰ ።
ደቂቅ ሊቁን እያፈሰ ፤
ያቀፉትን እየቀማ
ቀሪዎቹን እያመሰ ።
በዚህ ሁሉ ቁጣ መሐል
የኔ ማለፍ ወይም መትረፍ
መች ይታያል እንዳግራሞት ?
ሳላገኝሽ ብቻ እንዳልሞት ።

በእርግጥ ሞት የማይቀር ነው
ይሄን ነገር ስናስበው
ትንሽም ቢሆን አፅናኝ ነው ።
ያለ ፍርሃት እንዲሰው
ያስጎነጫል መሪር ሐሞት ፤
ሳላገኝሽ ብቻ እንዳልሞት ።

እንደ አጋፋሪ እንዳሻው
ውስጥ ለውስጥ በየ ዋሻው
በመንገድ ዳር ፥ በየ ጢሻው
ዕጣን ዣንጥላው ለታቦት
ለአዉልያ አርዳለሁ ጠቦት
ሳላገኝሽ ብቻ እንዳልሞት ።

By Hab HD

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19