Get Mystery Box with random crypto!

ቤተልሄም በ ኤልሳ ክፍል 3 ••••••••• ቤተልሄም ... ቤተልሄም ይል ይላ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ቤተልሄም


በ ኤልሳ

ክፍል 3


••••••••• ቤተልሄም ... ቤተልሄም ይል ይላል በህይወቱ እንደዚህ እንቆቅልሽ የሆነች ሴት ገጥማው አታውቅም ዝናዋ የልቡን የሆነ ክፍል ሲያጠምድ ይሰማዋል ወንድነትን የተላበሰ ሴትነቷ ገዝቶታል ቢሆንም ከሁሉም በፊት እሷን ወጥመድ ውስጥ ማስገባት እንዳለበት ያውቃል ግን ወጥመድ ውስጥ የምትገባ አይነት ቀሽም ሴት እንዳልሆነችም ያውቃል ህሊናም ብዙ ነግራዋለች ስለዚህ የመጀመርያ እርምጃዬ ከሷ ጋር መግባባት ይሆናል አለ ለራሱ ይህንን እያሰበ እንቅልፍ ወሰደው በማግስቱ ተነስቶ ስለ ቤቲ ማቀዱን ቀጠለ የመጀመሪያ ስራው ወሰ መስሪያ ቤቷ መሄድ ነበር ነገር ግን ሁለት ድርጅት እንዳላት የሰማው ትዝ ሲለው የትኛው ጋር መሄድ እንዳለበት ግራ ተጋባ ጠዋት የምትገባበትን ደውሎ የትኛው ጋር እንደምትገባ አረጋገጠ እና ዘንጦ መንገዱን ወደ መስሪያቤቷ አደረገ ....
..... ያለምንም ፈቃድ የ ቢሮዋን በር በርግዶ ገባ በዝምታ ትመለከተው ጀመር
" ይቅርታ የኔ ቆንጆ አረፍ ማለት ይቻላል?" እየተንተባተበ ... ያየውን ማመን አልቻለም ያ ትላንት ተጥሎ በ ከለላ ሲያየው የነበረ ውበት ዛሬ በ ኮስሞቲክስና በ ውብ ቀሚስ ታጅቦ ሲመለከት ያየውን ማመን ተሳነው ወምበሩን በ እጁ እየዳበሰ አይኑን ሳይነቅል ተቀመጠ
" ተቀመጥ እኮ አላልኩህም ?"
"አይኖችሽ ይናገራሉ"
" አይን የማምበብ ችሎታው እንኳን ያለህ አትመስልም"
"እንዴት እንደዛ ልትይ ቻልሽ"
" ምክንያቱም ችሎታው ቢኖርህ አይኖቼን አይተህ ትወጣ ነበር"
"ይሄንን የመሰለ ውበት ለማን ነው ጥዬ የምወጣው?"
"ለራሴ! ሰው አያስፈልገውም!"
"ይሻላል? "
"አዎ ምን እግር ጣለህ? "
"አይ አለፍ ስል በዛው ሀይ ልበልሽ ብዬ ነው "
" እሺ አመሰግናለሁ"
" እና ማታ ተገናኝተን ሻይ ቡና ብንልስ?"
"ማታ ላይ ሻይ ቡና ነው? ወይስ ራት የሚባለው?" የ ምፀት ፈገግታ ፈገግ እያለች
" እራት !" ከ አግራሞት ፈገግታ ጋር
" መልካም! ደስ ካለኝ እደውልልሀለሁ"
"ካላለሽስ?"
" እንደሙዴ".........
"መልካም ማታ ትላንቱ ሆቴል እጠብቅሻለሁ"
"እንደዛ አይነት ቦታ አይመቸኝም ይቅርታ!"
"እሺ የት ነው የሚመችሽ?"
"እኔንጃ ብቻ የሚመቸኝ ቦታ ያንተ መኖር ከተመቸኝ ደውዬ አገኝሀለሁ"
"እሺ እጠብቃለሁ"
" አሁን ስራ ላይ ነኝ ከይቅርታ ጋር..."
"እሺ አመሰግናለሁ" ብሎ ወጣ እና የ ፀሀፊዋን ስልክ ተቀብሎ ምሳ ሰአት ላይ ቀጥሯት ሄደ....
ምሳ ሰአት ላይ ከቀጠራት ከፀሀፊዋ ጋር ተገናኝተው ስለ ቤቲ ማውራት ጀመሩ
" እና ስራ ቦታ ምን አይነት ባህሪ አላት? "
" ተግባቢ አይደለችም!"
"ማለት? "
"በቃ በጣም ኮስታራ ናት በ ሳምንት ሁለት ወይም 3 ቀን ነው ስራ የምትገባው እነዛን ቀናት ግን በደምብ ትቆጣጠረናለች እንግዶችን ሁሉ ቀጠሮ የማሲዘው ለነዛ ቀናት ብቻ ነው "
"እና ኮስታራ ናት እያልሺኝ ነው?
" አዎ"
"እሺ እሺ ሌላስ ስለሷ የምትነግሪኝ ነገር አለ ስለሷ?"
"ኧረ ምንም የለም ቆይ አንተ ግን ለምን ማወቅ ፈለክ ስለሷ?"
"እሱ ያንቺ ጉዳይ አይደለም" ብሎ ጠረጴዛው ላይ የታሸገ 10 ሺ ብር አስቀምጦላት ተነስቶ ሄደ
"የማታ እንጀራ ይሉሀል... ይሄ ነው! " ብላ 10 ሺ ብሯን አንስታ ሂሳብ ከፍላ ወጣች ናሆም የተቻኮለው ያለ ምክንያት አልነበረም ቤቲ ከስራ ስትወጣ ስላያት ለመከተል ነበር እናም መኪናዋን ተከትሏት የቤቲን መኖሪያ ቤት አወቀ ስትገባ አያት "ወይ ሴት እና ውበት? " ብሎ ለራሱ ተገረመ እስክትወጣ ብዙ ቢጠብቅም በጣም ቆየች ከስአት ስራ እንደማትገባ በ ሰአቱ አረጋግጧል ውስጥ ገብታ ቆይታ ይሆናል ብሎ ለመመለስ ሲያመነታ ድንገት የውጪ በራቸው ተከፍቶ ቤቲ ስትወጣ አያት ያየውን ማመን አቃተው ቅድም ጉልበቷ ድረስ ቀሚስ ሄል ጫማ ኩል ሊፒስቲክ ሳምሶናይት እጇ ላይ ያየባት ልጅ አሁን ስትወጣ ፍሪዝ ፀጉሯ ግምባሯ ጋር ተይዟል ረጅሙ ፀጉሯ ወደላይ ተይዞ ግምባሯ ላይ ተበትኗል ሊፒስቲኳ የለም ከላይ ባለኮፍያ ረጅም ሹራብ ከስር የተቦጨቀ ጥቁር ሱሪ እና ስኒከር አድርጋ ሲጋራ እየለኮሰች ከቤቷ ወጣች አይኑን ማሸት ጀመረ የሚያውቃት ቤቲ አልመስልህ አለችው በርግጥ ከትላንቱ ማንነቷ ጋር ብዙም ለውጥ የለውም ቅድም ካያት ጋር ግን እህቷ እንኳን አትመስልም ቅርፁዋ ውበቷ ሁሉ የተደበቀ ሆነበት ያም ሆኖ ታምራለች እንደምታጨስ ግን አያውቅም ነበር ወዲያው እንቅስቃሴዋን መከታተል ጀመረ እናም ጥቂት ተራምዳ ከሰፈሩ ጎረምሶች ጋር ሰላም ተባብላ ተቀላቅላቸው መሳቅ መጫወት ጀመረች ስትስቅ ለመጀመሪያ ጊዜ አያት በጣም ነው የምታምረው ወዲያው ወደቤት ተመልሰው ገብተው ሁሉም በመኪና ወጡ ሾፌሯ ቤቲ ናት መኪናቸውን ተከትሎ ሲሄድ አንድ ግሮሰሪ ማረፊያው አደረገ ሲገቡ ሳያዩት ተከትሏቸው ወደ ውስጥ ገባ •••••••••

.......... ይቀጥላል........

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19