Get Mystery Box with random crypto!

1. የተነቃነቀን አጠበቅን ብለው የሚቀጠቅጡት በሀገሬው ምድር ህፃንን አብዝተው ወልደው ያላረጡት። | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

1.
የተነቃነቀን አጠበቅን ብለው የሚቀጠቅጡት
በሀገሬው ምድር ህፃንን አብዝተው
ወልደው ያላረጡት።
ከጨቅላ መንጋጋ የእናት ጡት ወትፈው
ለቅሶን ሚያስታግሱ
መመገቢያ ቋቱን እሬት እየቀቡ ድግስ የደገሱ።
አፈር ስሆን ብለው በጥቅልል እንጀራ
ሚያጣድፉ ጉርሻ
ለታይታ ለወሬ እህል ለሚዘሩ በደረቀ እርሻ

እናመሰግናለን!

2.
ለፈሰሰ እንባ ከንፈር ተመጦለን አለሁኝ ለሚለን
አባሽ ያጣ አይን ደም ለብሶ ደም ቢያለቅስ
ዞር ብሎ ላላየን።
ለመሸበት ሯጭ አዳር ፈቅደውለት እንቅልፉን ቢያሸልብ
ከመተኛው ስፍራ ባንድ ከፍተውበት
ቀልቡን ላሳጡት ልብ።

እናመሰግናለን!

ዮኒ
ኣታን @yonatoz

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19