Get Mystery Box with random crypto!

ቤተልሄም በ ኤልሳ ክፍል 8 ••••••••••••••••• እየተሳኩላት ይመስላል | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ቤተልሄም


በ ኤልሳ

ክፍል 8

••••••••••••••••• እየተሳኩላት ይመስላል ወዲያው ቅርብ ጓደኞቿ ጋር ደውላ ወጥተው እንዲጠብብቋት እና ፈታ እንዲሉ ነገረቻቸው ከነዛ ውስጥ አንዱ ልዑል ነበር
°°°
ናሆም እቤቱ ገብቶ ስለ ቤቲ ማሰብ ጀመረ ቅድም ሲያቅፋት የተሰማው ስሜት ማንንም ሲያቅፍ ተሰምቶት አያውቅም በሆነ በተለየ መንገድ ልቡ ውስጥ እንደገባች ገብቶታል በየቀኑ ሴት ሲያፈራርቅ የነበረው ናሆም ዛሬ ከቤቲ ሌላ የሴት ስልክ ማንሳት አስጠልቶታል ለመጀመሪያ ጊዜ የህሊና ፀፀት ውስጥ ገብቷል ከራሱ እና ከማይደራደርበት ክብሩ የበለጠ ቦታ በህይወቱ ላይ ሲሰጣት ይታወቀዋል በጣም በጣም!......
ሌላኛው ቀን ነጋ የቀኑን መንጋት አስተውሎ ሳይጨርስ ሰአቱን ሲያይ ረፍዷል በፍጥነት ተነስቶ ስራ ቦታ ሄዶ የትላንቱንም ጭምር ስራውን ሲሰራ ዋለ በጣም ቢዚ ስለነበረ ስለሌሎች ነገሮች ማሰላሰያ ጊዜ አልነበረውም ምንም ሳያርፍ መሸ 12:30 ሆነ 1:30 ላይ ቢሮውን ዘግቶ ወጣ ማንንም ሳያገኝ ቤቱ ሄዶ ለማረፍ ቢሞክርም አልተሳካለትም ቤቲን ሳያገኛት ሳያያት መዋሉ ረብሾታል ከቀኑ ውስጥ የሆነ ነገር እንደጎደለ ተሰማው እንደ ትራ ለመቁጠር ቢሞክርም አልተሳካለትም..... መኪናውን አስነስቶ ቤቲ ጋር መሄድ ጀመረ
°°°
ቤቲ ቤት ከገባች ቆይታለች ራቷን በልታ ወደ መኝታ እየሄደች ነበር ድንገት ከውጪ ክላክስ ሰማች ወዲያው በ ፎቁ መስታወት ስታይ የናሆም መኪና ነበር ሁኔታው ቢያስፈራም አማራጭ ስለሌለ መክፈት ነበረባት ወዲያው የውጭው በር በእጅ መንኳኳት ሲጀምር ወጥታ ከፈተች ከኋላዋ ሽጉጧን ይዛ ነበር ልክ ስትከፍት ሰላም እንኳን ሳይል አቀፋት በሁኔታው ብትደናገጥም ምንም እንዳልተፈጠረ ሲያቅፋት አቀፈችው። ረጅም ሰአት ቆይተው ተላቀቁ .....
"ምን ሆነህ ነው በዚህ ሰአት?"
"ና... ናፈቅሺኝ " ቁና ቁና እየተነፈሰ
"ምን?" እየሳቀች
"አዎዋ ዛሬ እኮ አልተገናኘንም"
"ታዲያ ሳንገናኝ ብዙ አመታትን ኖረን የለ እንዴ ? "
"ላልውቅሽ አዎ"
"እሺ አሁን አገኘኸኝ ይኸው "
" እሺ......................ልሂድ?"
"አዎዋ መሽቷል እኮ"
"ህህህ ታዲያ ሲመሽ እኮ ግባ መሽቶልሀል እደር ነው የሚባለው
"እንዴ ገና ነው እኮ ብላ የእጅ ሰአቷን አየችው••••••••••

•••••••••••••"እንዴ ገና ነው እኮ ብላ የ እጅ ሰአቷን አየችው 3:47 ይላል
" ኦ ይቅርታ በቃ ደህና እደሪ እወድሻለሁ" ብሎ ተሰናብቷት ሄደ ብዙም ሳትቆይ ለህሊና ደወለችላት
"ሄሎ"
"ወዬ ህሉ ስሚማ ቅድም ኮ ሰውዬያችሁ መጣልሽ"
"መቼ ቅድም ማለት?"
"በቃ አሁን በይው"
"ቆይ ምን ሊሰራ"
"ናፈቅሽኝ ብሎ ...ሀሀሀ"
"ከምር?"
"አዎዋ"
"ዋው ይገርማል"
"ምኑ ነው የሚገርመው?"
" ናሆም ለሴት ልጅ እንደዚህ ሆኖ አያውቅማ"
"ሀሀ ለማንኛዋም ሴትማ እንደማይሆን ነግሮኛል "
"እና"
"እናማ እኔም ማንኛዋም ሴት እንዳልሆንኩ ነሬው ነበር"
"ሀሀሀ ደስ ትላላችሁ እውነት እና አንቺስ ለሱ ምንም ስሜት የለሽም?
"ማለት ምን አይነት ስሜት?"
"  ምን አይነት ልበልሽ እሱ ላንቺ የሚሰማው አይነት ስሜት ነዋ"
"እንደዛ አይነት ስሜት እንኳን የለኝም"
"እና ምን አይነት ስሜት ነው ያለሽ?"
"በቀል!"
"እ?"
"አይሰማም?"
"ኧረ ይሰማል ማለቴ ለምን? ናሆሜ ምን አደረገሽ?"
"እሱን ባካል እናወራለን"
"እሺ ግን......"
"ግን ምን?"
"አይ ምንም በቃ እናወራለን "
"እሺ ....መልካም አዳር "
"እሺ ደህና እደሪ" ህሊና ጭንቅላቷ ሁለት ሲከፋፈል ይሰማታል ናሆም የፈለገውን ቢደረግ ጉዳዩዋ አይደለም ምክንያቱም የስንት ሴት እምባ ምክንያት እንደሆነ ታውቃለች ግን ከቤቲ ጋር ያገናኘው ጉዳይ ምን እንደሆነ ግን ለማወቅ ጓጉታለች•••••••••••••••



.......... ይቀጥላል........

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19