Get Mystery Box with random crypto!

ቤተልሄም በ ኤልሳ ክፍል 7 •••••••••••• 'ፊሊጶስ ይባላል በጣም ነው | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ቤተልሄም


በ ኤልሳ

ክፍል 7


•••••••••••• "ፊሊጶስ ይባላል በጣም ነው የምወደው እናትና አባታችን ልጅ እያለን ነው በመኪና አደጋ ህይወታቸው ያለፈው ሁለቱም በአንድ ቀን ፊሊ ታላቄ ነው እሱ ነው እናትም አባትም ሆኖ ያሳደገኝ እኔንጃ ከሱ ሌላ ሰው ያለ ራሱ አይመስለኝም ነበር ሁሉንም ነገር የማቅደው የማልምመው ወደፊቴ ሁሉ ከሱ ጋር ነበር በቃ ህይወታችንን በሙሉ ፍቅር መኖር ጀመርን አለም ለኔ ያለሱ ባዶ ፍቺ ናት እናም በ አንድ ጎዶሎ ቀን ፊሊ እንደወጣ ቀረ ጭራሽ ያለልማዱ አደረ በማግስቱ ጓደኞቹ ደውለው መኪናው ውስጥ በ ሽጉጥ ተገሎ መገኘቱን ነገሩኝ በቃ ከዛ ቦሀላ ያለውን ማስታወስ አልፈልግም "
"ንገሪኝ"
"ምን ልንገርህ ? "
"በ ፖሊስ ምናምን ገዳዩን ለማግኘት አልሞከርሽም?
"ባስፈልግ ምን አመጣለሁ?
"ማለት?"
"አሁን ገዳዩን ባካል ባገኘው ወንድሜን ይመልስልኛል?
"እ..እሱማ...."
"ንገረኝ ፊሊን ይመልስልኛል ወይ? ጣፋጭ ልጅነቴን መመለስ ይችላል? ሳቄን መመለስ ይችላል? አሳዳጊዬን ፍቅሬን ህይወቴን መመለስ ይችላል? ንገረኝ ይችላል ወይ? የሸሚዙን ኮሌታ ይዛ እየ ወዘወዘች
"አ..አ...አይመልሰውም" እያያት እምባው መንታመንታ ይወርዳል
" እ..እ..እ እየኝ እሲ በደምብ እየኝ አይኔን እየኝ!" እየተቅለበለበች
በፈዘዘ እና በደከመ አስተያየት እምባ ባዘለ አይን አያት
"እ.እ.እብድ ነኝ አይደል እ? እብድ ነው አይደል የምመስለው?" እምባ ባዘለ አይን እየሳቀች
"አይደለሽም ቤቲ"
"ነኝ ነኝ እንጂ"
"ኖ ቤቲ"
"ምንም ም ..ም..ምንም አታስተባብልልኝ ብላ የያዘችውን ሲጋራ ምጋ በረጅሙ ተነፈሰች ናሆም ሊያቅፋት እጁን ያነሳና የሆነ ስሜት ሲከለክለው ይሰማዋል ድንገት እምባ ካይኖቿ ጉንጯን ሳይነካ ሲፈስ አየ ላለማየት ፊቱን ለማዞር ቢሞክርም አልቻለም ዞሮ እምባዋን እየጠራረገ ጭንቅላቷን ወደ ደረቱ አስጠግቶ አቀፋት ጥርሷን እየነከሰች ወገቡን ስታቅፈው ድንገት እጇ ወገቡ ላይ አስሮት የነበረው ሽጉጥ ላይ አረፈ••••••••••••••••
••••••••••••••• እጇ ወገቡ ላይ አስሮት የነበረው ሽጉጥ ላይ አረፈ ደንግጣ እቅፋን ለቃ ወጥታ በ ጥርጣሬ እና ፍርሀት አይን አየችው ሁኔታው ስለገባው "it's okay የኔ ቆንጆ ለጥንቃቄ ነው " ብሎ ስቦ እቅፋ ውስጥ አስገባት ልቡን የደስታም የሀዘንም የፀፀትም ስሜት እየተሰማው ነው ውስጡ ተረብሿል ግን ደግሞ እሷን በ እቅፋ ማድረግ በመቻሉ ደስታ ተሰምቶታል የሁለቱም እይታ ከፊትለፊታቸው እየመጣ ወደ ገደሉ ወደሚወርደው ፏፏቴ ላይ አረፈ ረጅም ሰአት ፀጥታ በመካከላቸው ሰፈነ ነገር ግን ሁለቱም በውስጣቸው ይለፈልፋሉ ናሆም እንዲህ ይል ነበር "ምናለ ይወገድ ያልኩ ቀን አንደበቴን በቆለፈው እኔ እንደቀልድ ስላልታመነልኝ ብቻ ያስወገድኩት ፊሊጶስ ለብዙዎች መኖር መሰረት በተለይም ለተሸነፍኩላት ሴት ህይወት መበላሸት ምክንያት ሆኗል ምናለበት እሱ ይሙት ያልኩ ቀን እኔኑ ቢደፋኝ የሸወደኝን ገንዘብ እኮ ተቀብዬው ማሳሰር ወይም መማር እችል ነበር አጉል እቀጣለሁ ብዬ በ እድሜ ዘመን ፀፀት ቀጣኝ.... አሁን ቤቲ እውነቱን ብታውቅ .... ለነገሩ ምንም አይፈጠርም እንዳዘነችበት እንጂ ልትገለው እንደምትፈልግ አንዴም አልነገረችኝም ቢሆንስ? ብትገለኝ ይሻለኝ ነበር የኔ እንደማትሆን ከምትነግረኝ። እውነት ራሱን አይሸሽግም ይባላል አንድ ቀን እውነቱን ማወቋ አይቀርም! ባታውቅስ እንዴት ነው እንዲህ እንደ ሸክም የከበደኝን ሀጢያት ተሸክሜ አብሬያት የምሆነው? እናንጃ!.... "እያለ የራሱን የተወዛገቡ ግምት እና ሀሳቦች መልሶ መላልሶ ራሱን ይጠይቃል።
ቤቲም በበኩሏ በውስጧ ታወራ ነበር ! ..
"ናሆም ይህ በቀል ቁጥር አንድ ነው አሁን ውስጥህን ምን እንደሚሰማህ አውቃለሁ ቻለው ናሆሜ ፊሊጶስን መግደል ከምታስበው በላይ ቀላል ሊሆን ይችላል የ ቤተልሔምን ወንድም መግደል ሲሆን ግን ዋጋው እጅግ በጣም ውድ ይሆንብሀል ለ እያንዳንዷ ድርጊትህ ከባድ ዋጋን ትከፍላለህ!......" ትል ነበር ድንገት ቀና ብላ
"በቃ እንሂድ ወይሻልም?" ስትለው ተገጣጠሙ.... ሊስማት ሲጠጋት ተነስታ ጥላው ሄደች በሆነው ነገር ግራ ገባው እና ወዲያው እንደቸኮለ ሲገባው በራሱ አፈረ።
ተከትሏት ከሄደ ቦሀላ በመኪና ቤት አድርሷት ብቻውን መመለስ ጀመረ ቤቷ ገብታ መጠጣት መጨፈር ጀመረች ነገሮች እየተሳኩላት ይመስላል••••••••

.......... ይቀጥላል........

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19