Get Mystery Box with random crypto!

ቤተልሄም በ ኤልሳ ክፍል 6 ••••••••••• ምን ይመስልሀል?' 'በምን አይ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ቤተልሄም


በ ኤልሳ

ክፍል 6


••••••••••• ምን ይመስልሀል?"
"በምን አይነት መልኩ ነው ይምናደርሰው?"
"ቀላል ነው በሆነ ነገር መምታት ወይንም የሆነ ነገር ላይ እንድትወድቅ በማድረግ"
"አይሆንም በፍፁም እሷ ህይወት ላይ አደጋ የሚያመጣ ምንም አይነት ነገር ማድረግ አልፈልግም"
" አለበለዚያ ያንተ ህይወት አደጋ ላይ ይወድቃል"
"አታስጨንቀኝ ያሬድ ያንን ማድረግ አልችልም"
"እሺ !"
"አሁን ብቻዬን መሆን እፈልጋለሁ"
"መልካም አስብበት ናሆም በደምብ አስብበት"
"እሺ" ብሎ አሰናበተው ብዙም ሳይቆይ ከ ቤቲ ጋር መግባባት የሚችልበት ትልቅ ሀሳብ መቶለት ሳይታወቀው "የስስስስስስ....." አለ
ሀሳቡም ይህ ነበር ቤቲ ከሱ ድርጅት ጋር ተመሳሳይ ስራ ያለው ድርጅት ስላላት በጋራ ለመስራት የ ስምምነት ውል ማስፈረም ነበር። ከዚያ ምናልባት ቤቲን በተለያዩ ምክንያቶች ማግኘት ለሱ ቀላል ይሆናል ....
°°°
ቤቲ ሁሉንም የሚወራውን ነገር እየሰማች ነበር ምክንያቱም ጠዋት የለበሰውን ልብስ እስካሁን አልቀየረም ወዲያው ስልኳ ጠራ ናሆም ነበር ።
"ሄሎ "
"ሄሎ ቤቲ "
"አቤት"
"ለ አንድ ጉዳይ በጣም ፈልጌሽ ነበር ቢሮ ልምጣ?"
"አይ ስራ አልገባሁም"
"ተገናኝተን ማውራት እንችላለን?"
"አይ አይመቸኝም "
"ግዴለም አንዴ ብቻ"
"ጥሩ በስልክ ንገረኝ"
" እሺ እየውልሽ አንዱ ድርጅቴ ካንቺ ድርጅት ጋር ተመሳሳይ ስራ ነው ያለው እና እዛ ያንን በጋራ ስምምነት እንድንሰራ ፈልጌ ነበር እንደ ሀሳብ ነው"
"አስቤበት መልስልሀለሁ "
"እሺ የኔ ቆንጆ እና ስራ ካልገባሽ ሻይ ቡና ብንልስ?"
" ደስ ይለኛል"
"እሺ ምሳ ሰአት ላይ ቤት እመጣለሁ"
"እሺ እጠብቃለሁ"
"እሺ ቻው "
"ቻው"
ስልኩን ዘግታ ወደቤት መሄድ ጀመረች የዱርዬ አለባበሷን ለብሳ ጠበቀችው ምሳ ሰአት ላይ መጥቶ ወሰዳት እና ምሳ በሉ 8 ሰአት ተኩል አልፏል "ከዚህ ቦሀላ የት ነው የምታሳልፈው? "
"ያው ቤት "
" አንድ ቦታ ልውሰድህ?"
"በጣም ደሲለኛል" በደስታ ፊቷን እያየ
"ስለዚህ እንሂድ " ብላው መኪናውን ከፍታ ገባች እሱም ገብቶ ወደምትመራው አቅጣጫ እያሽከረከረ ከ አዲስ አበባ ወጡ •••••••

••••••••••• ከ አዲስ አበባ ወጡ እና አንድ ሜዳ ላይ አስቆመችው ናሆም ሁኔታውን ፈርቶታል ሽጉጡን ዳበሰው ወደ አንድ ጫካ እየወሰደችው ነበር ጫካው አረንጓዴ ሆኖ አጠር ያለ ነው ጥቂት ተራምደው ከ ጫካው ሲወጡ አንድ ገደል ጫፍ ላይ ደረሱ እና ቤቲ ቀድማው ሄዳ አንዱ ድንጋይ ላይ ተቀመጠች እየተሰማው የነበረው መጠራጠር ለራሱም ገረመው 'ቤቲ እኮ እኔ እንዳስገደልኩት አታውቅም ምንድነው የሚያስፈራኝ ብሎ ሽጉጡን በደምብ ወደውስጥ ገፋ አድርጎ ሄዶ ከጎኗ ተቀመጠ ስፍራው ከሚባለው በላይ ውብ ነበር በህይወቱ አይቶት አያውቅም አለ ብሎም አያስብም ያውም እንደዚህ ቅርብ ቦታ ከፊት ለፊታቸው ያለችው ፀሀይ የ ልግባ አልግባ ትግሏን ተያይዛው ደም መስላለች ከፊት ለፊታቸው ትልቅ የ አለት ተራራ ከቧቸዋል ፊትለፊት ወደታች የሚፈሰው ነጭ ፏፏቴ ልቦናን ይሰርቃል ለጊዜው ሁለቱም በ ቦታው ውበት ተማርከው ዝም አሉ ጥቂት ቆይቶ ግን ናሆም ዝምታቸውን ሰብሮ ገባ
"እዚህ ቦታ ብዙ ጊዜ ትመጫለሽ?"
"አዎ በጣም ብዙ ጊዜ"
"መቼ መቼ"
"ብቸኝነት ሲሰማኝ"
"እና ዛሬ...?"
"አይ ዛሬ እንኳን ላሳይህ ነው"
"በጣም ደስ ብሎኛል በጣም ያምራል ! ደምበኛ እሆናለሁ" ከ ለስላሳ ፈገግታ ጋር
"አዎ በጣም ቆንጆ ቦታ ነው"
"ልክ እንዳንቺ "
"ኧረ ከሰው ውበት ጋር ይወዳደራል ብዬ አላስብም"
"እውነት ነው"
"እና እኔ ሰው አይደለሁ እንዴ?"
"አደለሽም"
"እና ምንድነኝ ?"
" መልአክ "
"እንዴት እንደዛ ልትል ቻልክ ?"
"በቃ ውበትሽ ተፈጥሮሽ ፀባይሽ"
"ተፈጥሮና ፀባዬን በምን አወክ?"
"ወፏ ነግራኝ"
"ወፌ ሁልጊዜ ልክ ናት ብለህ ታምናለህ?"
"አዎ ምነው ልክ አይደለችም እንዴ?"
"ሰሙን ናት ወርቁን ነው እንጂ "
"ስለዚህ መልአክ ነሽ ያልኩት ልክ ነኝ"
"ከከፍታዬ ወድቄ ሰይጣን ሳልሆን በፊት" ድምፅዋን ቀንሳ
" እ?"
"እ?"
"ምን አልሺኝ?"
"አይ መልአክም አይደለሁም ሰው ነኝ ነው ያልኩህ"
"ይሁንልሽ እሺ........... እና ስለ ቤቲ ንገሪኝ እስቲ?"
"ስለ ቤቲ ምን?"
"ለምንድነው የምታጨሽው?"
"በቃ ለጊዜውም ቢሆን ለህመሜ ማደንዘዣ ስለሚመስለኝ"
"ምንድነው ህመምሽ?"
"ወንድሜ!" ድንገት ተፈጥሮ ላይ ፈዞ የነበረ ፊቱን ወደሷ እያዞረ
"ወንድምሽ ምን? .... ማ...ማለቴ ወንድም እንዴት ህመም ይሆናል?"
" እንደዚህ!"
"አልገባኝም?"
"ፊሊጶስ ይባላል••••••••••••••



.......... ይቀጥላል........

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19