Get Mystery Box with random crypto!

(እግዜር አሳዘነኝ..) ============= ከመንበሩ ወርዶ ከከፍታው አንሶ በራፋችን ሲገኝ ስን | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

(እግዜር አሳዘነኝ..)
=============

ከመንበሩ ወርዶ ከከፍታው አንሶ
በራፋችን ሲገኝ
ስንጠራው በለቅሶ...

ያፈሰስነው እምባ ጥቂት ሳይታበስ
ሀጢአት አገርሽቶ
ግብራችን ሲራከስ
እያዘነ ዳግም ወደላይ ሲመለስ...

ጥበቃው ሳያንሰው
መመገብ መፍጠሩ
ለዘመናት ሳይደክም
እኛኑ ፍለጋ በእንግልት መኖሩ
አያሳዝንም ወይ
አንዳንዴስ እግዜሩ ???

#Da_kiyorna

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19