Get Mystery Box with random crypto!

ሠዊ ከርቤና ዕጣን ንሰግድን. . . .ሳትረሽ ተዘክረን. . . . እያልሽ ጨክኖ እንዳይቀጣን እ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ሠዊ ከርቤና ዕጣን

ንሰግድን. . . .ሳትረሽ
ተዘክረን. . . . እያልሽ
ጨክኖ እንዳይቀጣን
እቴ ሙሽራዬ ፥ ሠዊ ከርቤና ዕጣን
ምህረት ይሰጥሻል
ደግ ነው ሙሽራሽ ፥ አንቺን ይሰማሻል

ለተኩላው አበጋዝ ፥ ብሆንም ምርኮኛው
የመቅደሱ ሽታ ፥ ጢሱ የማጠኛው
ከሩቅ እየጠራኝ ፥ አስችሎኝ መች ተኛው
እቴ ሙሽራዬ ፥ ሠዊ ከርቤና ዕጣን
ከሃጥያት ቀንበር ፥ ነፃ እንዲያወጣን
ከፀጋው ግምጃ ቤት ፥ ፈልጎ እንዳያጣን

ሊቅ ያልተረጎመው ፥ ጠቢብ ያልደረሰው
ብዙ ሚሥጥር አለ ፥ ዕጣንሽ የያዘው
ሁለ መናሽ ታምር ፥ ቅኔ ነሽ ሰዋሰው
እቴ ሙሽራዬ ፥ ሠዊ ከርቤና ዕጣን
ይሁን እጅ መንሻ ፥ ለንጉስሽ ሥልጣን

አቤል ታደለ

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19