Get Mystery Box with random crypto!

#የፍቅር_ጊዜ ብዙዎች ይላሉ... ሳያት ነው የወደድኳት በልቤ የሳልኳት እሷ ልጅ የኔ ናት። | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

#የፍቅር_ጊዜ

ብዙዎች ይላሉ...
ሳያት ነው የወደድኳት
በልቤ የሳልኳት
እሷ ልጅ የኔ ናት።

የእኔው ግን...
ሳላያት፥ በመስማት ወደድኳት
ለእምዬ ማርያም፥ አታሳጪኝ አልኳት
ቦታዋን ሰጠዃ።
...
ግን ምን ሊያደርግ...
ምኗንም ሳላስቀር፥ ብወድላት እንኳ
በሯን ዘጋችብኝ፥ ልቤ ልቧን ሲያንኳኳ!

Meku Mura

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19