Get Mystery Box with random crypto!

ከኦሪት ዘፍጥረት እስከኛ መለያየት ቀራንዮ ነሽ! አለኝ በቃሉ ሰቀለኝ አንቺ የሁሉ ምክንያት ጎልጎ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ከኦሪት ዘፍጥረት እስከኛ መለያየት

ቀራንዮ ነሽ! አለኝ በቃሉ ሰቀለኝ
አንቺ የሁሉ ምክንያት ጎልጎታዬ
አይን አይኔን እያዬ
አንቺ ለኔ ሄዋኔ
ትእዛዝ የጣስኩልሽ ቃልን የሻርኩልሽ
ሎሌሽ ሆኜ የታዘዝኩሽ
ፈጥሮኝ ፈጥሮሽ ከሱ በላይ የምሰማሽ
ሰርክ ለኔ የምጠራሽ።
እሱ፤
ላቤን ጠብ እንዳደርግ
ለፍቼ እንድበላ ጨክኖ የፈረደው
ጣር ስቃይ ለግሶሽ
ምጥሽን ያበዛው እንደምን ቢነደው?
ዳሩ፤
ለምን አይብሰለሰል እንደምን አይነደው?
የሞት ሞትን ትሞታለህ
የሚል ማስጠንቀቂያን
እንካ በሚል ቃልሽ
ብላ በሚል ቃልሽ አለቅጥ ስንደው
እንደምን አይነደው
እሱ፤
ብቻዬን እሆን ዘንድ ፍፁም ያልወደደው።
አንቺ ፍጡር አንቺነትሽ በኔ ነሁላላነት
ብቻ አለመሆንን በማመን ሲንደው
ይህን ይሆን እንዴ
መፋቀር እያለ ሰው የሚነጉደው ?።
መልሺልኝ! አለኝ
አይ! አይመስለኝም አልኩት
ምን ነካኝ በሞቴ የቱን ያህል ከፋኝ
ለምን ተቃወምኩት?
ፊቱን ከሰከሰ
ድጋሚ ሰቀለኝ ድጋሚ በደልኩት።
በስንብት አይነት በጥልቀት አየሁት።

#በልጅ ብዕር Nebiyat Mulat

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19