🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ጉልበት ቆጥቢያለሁ (በእውቀቱ ስዩም) እንደ ልጅነቴ አክሮባት አልሰራ ልክ እንደታች አምናው ፥ ብ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ጉልበት ቆጥቢያለሁ
(በእውቀቱ ስዩም)

እንደ ልጅነቴ አክሮባት አልሰራ
ልክ እንደታች አምናው ፥ ብረት አልጠመዝዝ
ጠማማን አልገራ፥
ክንድ አልለካካ ፥ ከጎበዞች ጋራ
እግሬ አጭር ተራምዶ፥ በረጅሙ አረፈ
እግዜር እድሜ አይጨምር፥ አቅምን ካልሸረፈ : :

ልቦናሽ ታውኳል?
‘የፈራው ደረሰ
አቅሙ ተቀነሰ
ይስለመለም ጀመር፥
እንደ ቁራጭ ሻማ፥ በነፋስ ክንፍ ፊት እንደተለኮሰ ‘
የሚል ፍርሀት ይዞሽ
እንግድያውስ አይዞሽ!
የሌለን ቢመስልም፥
ሀይልና ወኔ አለን፥
የምናስቀምጠው፥ ለክፉ ቀን ብለን ::

ሲያምርሽ አፋፍሼሽ ፥
እስካልጋየ ድንበር
ሲያምሽ ተሸክሜሽ ፥
እስካምቡላንሱ በር
የምራመድበት
ጉልበት ቆጥቢያለሁ፥ ከቁንጮ እስከ ሽበት


ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19