Get Mystery Box with random crypto!

ተስፋ ነበረን ....... ሊያውም ከፀሀይ የሚያበራ ከጥልቁ ባህር የሚያስ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ተስፋ ነበረን .......

ሊያውም ከፀሀይ የሚያበራ
ከጥልቁ ባህር የሚያስፈራ
ከሰማይ ስባሪ የሚሰፋ
በአለም ፊት እኛን ያፋፋ
ተስፋ ነበረን:
ታሪካችንን የሚለውጥ
ወደሰማይ ስናንጋጥጥ
ህይወትን የሚያለመልም
አለም ነበረ የኛ ህልም።
ልናሳካው የፈለግነው
ልናጣው ያላቀድነው
ተስፋ ነበረን እኔና አንቺ
ለድካማችን አበርቺ።
ታድያ _ህልማችንን ሳንኖር አላማችንን ሳናሳካ
ደስተኝነትን ሳንጠግበው እንዳለምነው ሳንፈካ
ለምን ቶሎ ተሸነፍሽ???
እንደማላሳካው እያወቅሽ ለምን ትተሽኝ ከነፍሽ?
በየትኛው ጥንካሬ በየትኛውስ ትግስቴ ነው
የኔና ያንቺን በእውን እውን የማደርገው
ስደሰት_ስመለከትሽ
በህልሜ ስትመጪ_ ስሸሽ
እንዳሳካው ቃል የምታስገቢኝ
ምን አይተሽብኝ ነው ንገሪኝ ??!



ሩታ


ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19