Get Mystery Box with random crypto!

ዝምታ ''''''' ፀጥ እረጭ እፍንታ፣ ሳቅ የለ ጉምጉምታ፣ ወሬ የለ ጩኸት፣ አንተ ባለህበት፣ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ዝምታ
"""""""

ፀጥ እረጭ እፍንታ፣
ሳቅ የለ ጉምጉምታ፣
ወሬ የለ ጩኸት፣
አንተ ባለህበት፣

እርስ በርስ ምክክር፣
ተቃርኖ ክርክር፣
ፍቅርን መገላለፅ
ጥላቻን መናገር፣
አንተ ባለህበት....
ፍፁም አይሰማም
ድምፅ ብሎ ነገር፣

ስትኖር....
እርፍ ስንፍ
ላፍታ፣
ዘላለም የምትመስል
ትንሽዬ ደስታ፣
አጀብ የለ ወጀብ፣
በጥልቅ ሰላምህ
መሰለል መታጀብ፣

አንተ ባለህበት፣
የለብህ ሹም ሽረት፣
አዛዥ የለ አለቃ፣
አንተው የምታፈዝ
አንተው የምታነቃ፣
አትገኝም እንጂ....
ግዛትህ ተስፋፍታ፣
እልፍ ምዕመን ያለህ
ንጉስ ነህ ዝምታ።።


ኤዶምገነት ፃፈችው

@Edom_Ge

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19