🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ክፍል 4 & ምክንያታዊነት የሰውነት ትልቁ መገለጫ ነው፤ Yeshitla Yigezu #መ | 𝗖𝗵𝗿𝗶𝘀𝘁𝗶𝗮𝗻𝘀 𝗣𝗲𝗿𝘀𝗽𝗲𝗰𝘁𝗶𝘃𝗲𝘀 Archives

ክፍል 4

& ምክንያታዊነት የሰውነት ትልቁ መገለጫ ነው፤

Yeshitla Yigezu

#መሃመድ(ቡርሐን) አሊ ከ ቴዎድሮስ ተ/አረጋይ ጋር ፍልስምና 4 ላይ ሲወያዩ መሃመድ(ቡርሐን) እንዲህ ብሎት ነበር፣
“...ጭንቅላት ትልቅ ነገር ነው...ብዙ ጊዜ ትልቅ ሐሳቦች የሚወጡት ከተጨቆኑ ህዝቦች ነው። በአለም ላይ ትልልቅ አብዮቶች የሚወለዱት ከተጨቆኑ ህዝቦች ነው። ህመም ሲበዛ ነው መድሃኒቱ የሚፈለገውም የሚገኘውም...” ይህን ሃሳቡን እጋራለሁ። በአለም ላይ የሚታየውን ፈጣን እድገት ስናይ የሰው ልጅ ምን ያህል ግሩም አይምሮ የተቸረው እንደሆነ እናስብና ደግሞ እንዲህ በፍጥነት እያደገ ያለው የሰው ስልጣኔ ከሞራል መላሸቅ ጋር የተሟሸ ሲሆን ምን ያህል ጥበብ እንደሚያስፈልገን እንገነዘባለን። በህይወት ጥበብን ለማግኘት ከፈጣሪ መቸር እንዳለ ሆኖ፣ እኛም አይምሮኣችንን ነገሮችን በጥልቀት እንዲያስብ ማሰብ እንደሚገባን እንረዳለን።

“የአስተሳሰብ መሠረታዊያን”(The rule of thoughts or the rule of foundationalism) የሚባሉ በነባራዊ(በአይለወጤ) እውነታ ላይ የተንተራሱ የእሳቤ ህጎች አሉ። እነኚህ ህጎች የነገሮችን እውነታና የሰውን ሃሳብ በጥልቀት እንድንረዳ ፋይዳቸው ብዙ ነው። ከነዚህም ውስጥ፣

#የህላዌ ህግና የእራስነት ህግ(the law of existence and the law of identity):- ህልው(ያለ፣ "ለ"ሲጠብቅ) ነገር ያው ያለ ሲሆን፣ አንድ ነገር ያው አንድ ነገር ሲሆን፤ ለምሳሌ፣ "ሀ"፥"ሀ" እንጂ "ለ" ወይንም ሌላ ፊደል አይደለም። አንድ ሰው የራሱን መኖር ሊክድ አይችልም። ምክንያቱም የራሱን መኖር ለመካድ መኖር ስላለበት።

#ያለ መቃረን ህግ(the law of non-contradiction):- ይህ ህግ ደግሞ ተቃራኒ ነገሮች በአንድ አይነት ሁኔታና ጊዜ እውነትም ውሸትም ሊሆኑ አይችሉም የሚል ህግ ነው። ለምሳሌ፦ ሜሲ ለPSG ቡድን ፈርሟል። ይህ አ/ነገር በአንዴ እውነትም ውሸትም ሊሆን አይችልም። ክብ አራት ማዕዘን የሚባል ነገር አለ(ይሄም እርስ በእርሱ ይጋጫል።)

#የመንስኤ'ኣዊነት(አስገኚነት) ህግ(the law of causality)፦ ህልው ያልሆነ ነገር ህልው የሆነን ነገር አያስገኝም። ምንም ነገር የሆነን ነገር ሊያስገኝ አይችልም። ለተገኘ ነገር አስገኚ አለው። ያ አስገኚ(ህልው) አንጡራ(necessary being) ሊሆን ይችላል፣ ጥገኛ(contingent being) ሊሆን ይችላል።
#የመሃከሉን አስወጋጅ ህግ(the law of excluded middle)፦ ህልው ወይ ህላዌ አልባ።(Either Being or non-being)። ለምሳሌ፦ በመኖርና ባለመኖር መካለከል የሚባል የኗሪና ኢ-ነዋሪ መሃከለኛ የለም። በእውነትና ውሸት(እውሸት የሚባል )
መሃከለኛ የለም።

#የመሰካካት/የምስስል ህግ(the law
of analogy):- ውጤቱ ከአስገኚው ጋር የሚመሳሰልበት(similar የሚሆንበት) ህግ። ለምሳሌ፦ መልስ መልሱ የተገኘበትን አይምሮ ይመስላል።
ይቀጥላል...