Get Mystery Box with random crypto!

𝗖𝗵𝗿𝗶𝘀𝘁𝗶𝗮𝗻𝘀 𝗣𝗲𝗿𝘀𝗽𝗲𝗰𝘁𝗶𝘃𝗲𝘀 Archives

Logo of telegram channel christianperspe — 𝗖𝗵𝗿𝗶𝘀𝘁𝗶𝗮𝗻𝘀 𝗣𝗲𝗿𝘀𝗽𝗲𝗰𝘁𝗶𝘃𝗲𝘀 Archives 𝗖
Logo of telegram channel christianperspe — 𝗖𝗵𝗿𝗶𝘀𝘁𝗶𝗮𝗻𝘀 𝗣𝗲𝗿𝘀𝗽𝗲𝗰𝘁𝗶𝘃𝗲𝘀 Archives
Channel address: @christianperspe
Categories: Religion
Language: English
Subscribers: 233
Description from channel

Our theme: "let this mind be in you,which was also in Christ Jesus".
👉Sharing Ideas and Faith-Buliding songs
👉Inspritional Bible Quotes.
#CPmusic
#CPquote
#CPissue
Our discussion group @cpminglegroup

😉Join Our Channel
@ChristiansHiphop
@Ch_musix

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


The latest Messages

2021-08-29 18:22:57 2 ኛው አጫጭር ልብወለድ ታሪክ በሚመጣው ሳምንት ይለቀቃል በተለይ ለወጣቶች ይጠቅማል ብለን ያሰብነውን ይዘን እንመጣለን ይጠብቁን

@christianperspe
99 viewsN£h£mi@h, 15:22
Open / Comment
2021-08-24 12:43:44
Size -A3
Price- 600 ETB
Order- @WallartAmen

@wallartsethiopia
@wallartsethiopia
@wallartsethiopia
148 viewsAbraham A. , 09:43
Open / Comment
2021-08-21 11:48:40
Come & Move by Tribl & Maverick City Music (Ft. Joe L Barnes, Mariah Adigun & Ryan Ofei)

@ChristiansHiphop
223 views𝖅𝖊𝖗𝖚, 08:48
Open / Comment
2021-08-20 23:59:53 ክፍል 4

& ምክንያታዊነት የሰውነት ትልቁ መገለጫ ነው፤

Yeshitla Yigezu

#መሃመድ(ቡርሐን) አሊ ከ ቴዎድሮስ ተ/አረጋይ ጋር ፍልስምና 4 ላይ ሲወያዩ መሃመድ(ቡርሐን) እንዲህ ብሎት ነበር፣
“...ጭንቅላት ትልቅ ነገር ነው...ብዙ ጊዜ ትልቅ ሐሳቦች የሚወጡት ከተጨቆኑ ህዝቦች ነው። በአለም ላይ ትልልቅ አብዮቶች የሚወለዱት ከተጨቆኑ ህዝቦች ነው። ህመም ሲበዛ ነው መድሃኒቱ የሚፈለገውም የሚገኘውም...” ይህን ሃሳቡን እጋራለሁ። በአለም ላይ የሚታየውን ፈጣን እድገት ስናይ የሰው ልጅ ምን ያህል ግሩም አይምሮ የተቸረው እንደሆነ እናስብና ደግሞ እንዲህ በፍጥነት እያደገ ያለው የሰው ስልጣኔ ከሞራል መላሸቅ ጋር የተሟሸ ሲሆን ምን ያህል ጥበብ እንደሚያስፈልገን እንገነዘባለን። በህይወት ጥበብን ለማግኘት ከፈጣሪ መቸር እንዳለ ሆኖ፣ እኛም አይምሮኣችንን ነገሮችን በጥልቀት እንዲያስብ ማሰብ እንደሚገባን እንረዳለን።

“የአስተሳሰብ መሠረታዊያን”(The rule of thoughts or the rule of foundationalism) የሚባሉ በነባራዊ(በአይለወጤ) እውነታ ላይ የተንተራሱ የእሳቤ ህጎች አሉ። እነኚህ ህጎች የነገሮችን እውነታና የሰውን ሃሳብ በጥልቀት እንድንረዳ ፋይዳቸው ብዙ ነው። ከነዚህም ውስጥ፣

#የህላዌ ህግና የእራስነት ህግ(the law of existence and the law of identity):- ህልው(ያለ፣ "ለ"ሲጠብቅ) ነገር ያው ያለ ሲሆን፣ አንድ ነገር ያው አንድ ነገር ሲሆን፤ ለምሳሌ፣ "ሀ"፥"ሀ" እንጂ "ለ" ወይንም ሌላ ፊደል አይደለም። አንድ ሰው የራሱን መኖር ሊክድ አይችልም። ምክንያቱም የራሱን መኖር ለመካድ መኖር ስላለበት።

#ያለ መቃረን ህግ(the law of non-contradiction):- ይህ ህግ ደግሞ ተቃራኒ ነገሮች በአንድ አይነት ሁኔታና ጊዜ እውነትም ውሸትም ሊሆኑ አይችሉም የሚል ህግ ነው። ለምሳሌ፦ ሜሲ ለPSG ቡድን ፈርሟል። ይህ አ/ነገር በአንዴ እውነትም ውሸትም ሊሆን አይችልም። ክብ አራት ማዕዘን የሚባል ነገር አለ(ይሄም እርስ በእርሱ ይጋጫል።)

#የመንስኤ'ኣዊነት(አስገኚነት) ህግ(the law of causality)፦ ህልው ያልሆነ ነገር ህልው የሆነን ነገር አያስገኝም። ምንም ነገር የሆነን ነገር ሊያስገኝ አይችልም። ለተገኘ ነገር አስገኚ አለው። ያ አስገኚ(ህልው) አንጡራ(necessary being) ሊሆን ይችላል፣ ጥገኛ(contingent being) ሊሆን ይችላል።
#የመሃከሉን አስወጋጅ ህግ(the law of excluded middle)፦ ህልው ወይ ህላዌ አልባ።(Either Being or non-being)። ለምሳሌ፦ በመኖርና ባለመኖር መካለከል የሚባል የኗሪና ኢ-ነዋሪ መሃከለኛ የለም። በእውነትና ውሸት(እውሸት የሚባል )
መሃከለኛ የለም።

#የመሰካካት/የምስስል ህግ(the law
of analogy):- ውጤቱ ከአስገኚው ጋር የሚመሳሰልበት(similar የሚሆንበት) ህግ። ለምሳሌ፦ መልስ መልሱ የተገኘበትን አይምሮ ይመስላል።
ይቀጥላል...
129 viewsMoses Daniel, 20:59
Open / Comment
2021-08-19 16:23:29
ቃል በገባነው መሰረት አጫጭር ልብወለድ ታሪክ ይዘን መተናል ከታች ያለውን Audio ይክፈቱትና ይስሙት ከተመቻቹ share ያድርጉ,በቀጣይ ወጣታዊ ይዘት ያላቸው ታሪኮች ይዘን እንመጣለን ይጠብቁን: :
242 viewsN£h£mi@h, 13:23
Open / Comment
2021-08-18 00:30:48 ክፍል 3፣ #የሺጥላ ይገዙ

ምክንያታዊነት የሰውነት ትለቁ መገለጫ ነው::

#ራስን በራስ የመቃወም ሙግት(self-defeating or self-stultifying or self-refuting argument):- በግልፅም ሆነ በውስጠ ታዋቂነት እየደገፉ/እየተቃወሙ ያሉትን ሙግት መቃወም/መደገፍ።

#ለምሳሌ1፦ ሁሉም ሰው ውሸታም ነው። >>ይህ አ/ነገር እውነት ከሆነ፦ ራሱን ትክክል አድርጓልና ስህተት ነው። ውሸት ከሆነ የእውነት ፋይዳ ያለው አ/ነገር ሆኗልና ሁሉም ሰው ወሸታም አለመሆኑ አ/ነገሩን ውሸት ያደርገዋል።

#ምሳሌ2:- ፍፁም እውነት የለም። ወይንም እውነት ሁሉ አንፃራዊ ነው። 1) ይህ አ/ነገር እውነት ከሆነ፦ ከሱ ጋር እንድንስማማ ይህ ፍፁም እውነት ነው ተቀበሉት እያለን ስለሆነ ስህተት ነው።
2) ውሸት ከሆነ፦ የእውነት ፋይዳ ያለው አ/ነገር ስለሆነ ውሸት ነው።

#ምሳሌ3:- እውነት በውጤቱ ይረጋገጣል። ችግሩ፦ አ/ነገሩ እራሱ ስላልተረጋገጠ ውሸት ነው። ወይንም ገና ጅማሬው ላይ ሆኖ ፍፃሜው ላይ ነኝ እያለ ስለሆነ ዋሽቷል።(a means justifies an end እንጂ ተቃራኒው እውነት አይሆንም።)

#ምሳሌ4:- ሁሉም ነገር በአምስቱ የስሜት ህዋሳት ካልተረጋገጠ ውሸት ነው። ችግሩ፦ ይህ አ/ነገር እራሱ በአምስቱ የስሜት ህዋሳት ሳይረጋገጥ እውነት እንደሆነ ማሰቡ።

#ምሳሌ5:- በአምስቱ የስሜት ህዋሳት የማይረጋገጥ ነገር ሁሉ ትርጉም አልባ ነው። ችግሩ፦ ይህ አ/ነገር በአምስቱ የስሜት ህዋሳት የተረጋገጠ ስላልሆነ ትርጉም አልባነቱን ራሱ በራሱ ላይ መናገሩ።

#ምሳሌ6:- ስለ ምንም ነገር እርግጠኛ መሆን አንችልም። ችግሩ፦ ስለ ምንም ነገር እርግጠኛ መሆን አንችልም ስላለው አ/ነገር እርግጠኛ መሆኑ ራሱን በራሱ ይቃወማል።

#ምሳሌ7:- ሁሉም እምነት ውሸት ነው። ችግሩ፦ በመሰረቱ ይሄን አ/ነገር ባያምነውና እርግጠኛ ባይሆንበት እንድንቀበለው አያውጅም።(“...the tradition or standard definition of propositional knowledge is the view that knowledge is justified true belief...” Dr. William Lane Craig) ስለዚህ አ/ነገሩንም ጨምሮ ውሸት ሊሆን ነው ይህ ከሆነ ሰህተት ነው። ራሱን በራሱ እየተቃወመ ነው።
#ምሳል8:- ስለ ፈጣሪ መኖር/ህላዌ ማወቅ አንችልም። ችግሩ፦ ስለ ፈጣሪመኖር ማወቅ አለመቻሉን ማወቁ ራሱን በራሱ የሚቃወም ሙግት ነው።
#ምሳሌ9:- ሰለማምነው እምነት ምንም ማስረጃ ማቅረብ አይጠበቅብኝም። ችግሩ፦ ማስረጃ ማቅረብ እንደማይጠበቅበት ለማስረዳት ማስረጃ ማቅረቡ።
#ምሳሌ10:- ስለ ፈጣሪ መኖር ትሩጉም በሚሰጥ አ/ነገር ማውራት አንችልም። ችግሩ፦ ስለ ፈጣሪ መኖር ትርጉም በሚሰጥ አ/ነገር ማውራት አለመቻሉን ትርጉም በሚሰጥ አ/ነገር ስለ ፈጣሪ
ማውራቱ።
...ይቀጥላል...
215 viewsMoses Daniel, 21:30
Open / Comment
2021-08-17 02:10:27 ክፍል 2፣

ምክንያታዊነት(being reasonable) የሰውነት ትልቁ መገለጫ ነው::

“...ሰውን እንዲያስብ ልታደርግ ባትችልም፣ ማሰብ እንደሚችል ግን ልትነግረው ትችላለህ...” ከ‘ጥበብ ከጲላጦስ’ መፅሐፍ የተወሰደ። የሰው ልጆች መሆናችን የምንከተለውን፣ የምናምነውን፣ የምንፈልገውን ልንጠይቅ፣ ልናስብ፣ ልንመረምር ይገባል እላለሁ። የአለመኖር መፅሐፍ ደራሲ ዶ/ር ዳዊት በመፅሃፉ ባለው ገፀባህሪ እንዲህ ይለናል፣ “...‘ሰው በአጠቃላይ፤ የኛ ሃገር ደግሞ በተለይ፤ ለመኖር የተባለውን የሚቀበል ነው። ብዙ አይጠይቅም።’...” ለምን ይህ ይሆናል? ለምን በልዩነት ሃገሬ ላይ ይሄ አለመጠየቅና አለመመርመር በዛ? በኃላ ገፅ 107 ላይ እንዲህ ብሎ ወጣቶችን ይመክራል፣ “...በወጣትነትህ አንተ ላይ ያለው ሃላፊነት፤ ስለተባሉትና ስለተፃፉት ነገሮች ማሰብ ብቻ ነው...” መጠየቅ፣ማሰብ....

በዚህ ክፍል የምንዳስሰው፦ ሙግት፣ የሙግት ነጥብ፣ ድምዳሜ፣ አዋጅ፣ ምንጨታዊ ሙግት፣ መስተጋብኣዊ ሙግት፣ ርቱዕ ሙግት፣ ስሙር ሙግት፣ራስን በራስ የሚቃወም ሙግት፣ ተፋልሶ ምን እንደሆኑ በጥቂት ማብራሪያ እናያለን።(ከላይ የተጠቀምኳቸው አብዛኛዎቹ የስነ አመክንዮ ቃላትና ሃረጎችን የተዋስኩት ከዶ/ር ተስፋዬ ሮቤሌ “ስነ አመክንዮ” ከሚለው መፅሐፋቸው ነው። እንድታነቡት በትህትና እጋብዛችኀለሁ።)

#ሙግት(argument) ውበት ባላቸው አረፍተነገሮች የተዋቀረ፣ የመነሻ ነጥቦችና ድምዳሜ የተሰናሰለ ፍልስፍናዊ ውቅር ነው። ሙግት ሃሳባችንን በምክንያት የምንዘውርበት መንገድ ነው። ሙግት መደማመጥ የበዛበት የጠይቂዎች ሜዳ ነው። ሙግት ጭቅጭቅ፣ስድብ፣ እንካ ሰላንቲያ አይደለም። #የሙግት ነጥብ(premise) የእውነትነት ይዘት ያላቸው ድምዳሜውን የሚደፍፉ አ/ነገሮች ናቸው።#ድምዳሜ(conclusion) እውነትነት ያለው በሙግት ነጥቦቹ የሚደገፍ ወይም ስሙምነት ያላቸው አ/ነገሮች ናቸው።#አዋጅ(proposition) የእውነት ፈይዳን(truth value) ያቀፈ ማለትም እውነት ወይንም ሃሰት ሊሆን የሚችል አ/ነገር ነው።#ስሙር ሙግት(valid argument) በአሰካክ ሂደት የሙግት ነጥቡ የድምዳሜውን ሲያፀና(በዋናነት አሰናሰሉ ነው ሚታሰበው)።#ርቱዕ ሙግት(sound argument) የምንለው ደግሞ ምክኖዮኣዊ ስሙር ሲሆንና እውነት የሆኑ የሙግት ነጥቦች ሲኖረው ነው።#ምንጨታዊ ሙግት (deductive argument) የሙግት መነሻ ነጥቦች እውነትነት ለድምዳሜው እውነትነት ዋስትና ሲሰጠን ሙግቱን DA እንለዋልን። “the premises guarantee the truth of their conclusions.”Dr. William Lane Craig.#መስተጋብኣዊ ሙግት(Inductive argument) ከተቀናቃኝ ሙግቶች በላይ የሙግት ነጥቦቹ የድምዳሜውን እውነትነት ደረጃ ሲጨምሩ IA እንላቸዋልን።(የፍልስፍና ት/ት ቅፅ 1 ላይ፣ “ፍራንሲስ ቤከን...አርስቶትልን እንደወረደ ከመቀበልና DA ከመጠቀም ይልቅ የሙከራ ሳይንስን...እና IA
መጠቀም ተፈጥሮን ይበልጥ ለማወቅ እንደሚረዳ ተከራከረ...” ይሉናል። ከሆነ IA ያገኘው ፍራንሲስ ቤከን ነው።)#ራሱን በራስ የመቃወም ሙግት (self-defeating argument) ይህ ሙግት እየተቃወሙ ያሉትን ሃሳብ በግልፅም በውስጠ ታዋቂነትም መደገፍ፣ እየደገፉ ያለወንም ሃሳብ በግልፅም በውስጠ ታዋቂነትም መቃወም። #ተፋልሶ(fallacy) የሙግት ህፀፅ ማለት ሲሆን ብዙና ልዩልዩ ናቸው።

ከፍልስፍና ሀሁ መፅሐፍ የተወሰደ፣ “...ሶቅራጠስ ይጠይቃል፣ ከዚያም መልስን ያገኛል...” እንጠይቅ፣ እውነትን እንከተል። ይቀጥላል...

Yeshitla Yigezu
120 viewsMoses Daniel, 23:10
Open / Comment
2021-08-17 02:10:06 ምክንያታዊነት የሰውነት ትልቁ መገለጫ ነው፤
ምክንያታዊነት፦ ሰዎች እንደመሆናችን ከእንስሳት የምንለይበትና ክቡር ፍጡራን መሆናችን የሚንፀባረቅበት መንገድ ነው። ዶ/ር ተስፋዬ ሮቤሌ ስነ አመክንዮን እንዲህ ይፈቱታል፣ “ሥነ አመክንዮ ትክክለኛውን ሙግት ትክክለኛ ካልሆነ ሙግት የምንለይበት መርሖና ዘዴ፣ ምን እንደ ሆነ የሚያስተምረን የትምህርት ዘርፍ ነው።” እንዲሁም ይህ የትምህርት ዘርፍ የቀናውንና ስሁት የሆነውን ሃሳብ የምንመረምርበት፣ አመለካከታችንንና እምነታችንን በማስረጃና ተገቢ አ/ነገሮችን በመጠቀም ለሰዎች የምናቀርብበት፣ እይታችንን ለዛ ባለው መልኩ ማለትም ሊገመገም፣ሊተችና ተቀባይነት እንዲኖረው አድርገን የምናሰናዳበት ተግባቦት ከሳ("ሳ" ሲጠብቅ)ች ስልት ነው።

#ታላቁ ፈላስፋ አርስጣጣሊስ፣ ልክ አይሳክ ኒውተን የስበትን፣ የእንቅስቃሴንና የባለበት መቆምን ህግ እንዳገኘ(discover እንዳደረገ)፣ አርስቶትልም የአመክንዮን ህግ እንዳዋቀረ ይነገራል። እነኚህ ህጎች አለመፈብረካቸው(invent አለመደረጋቸው) ይልቁን መገኘታቸው በሰዎች መካከል ከጥንትም የነበሩ
እንደሆነ እና በፈጣሪ መኖር ለምናምን የፈጣሪ ስጦታዎች እንደሆኑ እናስተውላለን። ይህ ከሆነ ደግሞ አየርና ውሃን ለመኖር አስፈላጊ ሆነው በአግባቡ እንደምንጠቀማቸው ሁሉ እነኚህንም የአመክንዮ መርሆች በአግባቡ ልንጠቀማቸው ይገባል።

#የአመክንዮን ህግ መጠቀም ለምን ይጠቅማል?
1) ሃሳባችንን በአግባቡና በማስረጃ አስደግፎ ለሌላው ሰው በትህትና ለማስረዳት፣

2) የአብዛኛውን ሰው አመለካከት ለመገምገምና ያን አመለካከት የምንከተለውም የማንከተለውም ለምን እንደሆነ ምክንያታዊ ሆኖ ለመመላለስ፣

3) ከስሜታዊነት በፀዳ መልኩ የሌላውን ሰው እምነትና አመለካከት ለመመርመር፣ ለመገምገም፣ ለመቀበልና ለመተቸት(ትችት ስድብ አይደለም!)፣
4)ሰዎች በመሆናችን የተለያየ አስተሳሰብ፣አመለካከትና እምነት ስላለን ሊያግባባን የሚችል ብቸኛ "common ground" ስለሆነና ሌሎች የትየለሌ ጠቀሜታዎች አሉት።

#በግል እይታዬ ሰዎች ፈጣሪ የሰጣቸው ግሩም አይምሮ አላቸው። ያን አይምሮኣቸውን በሚገባ ቢጠቀሙት የምንኖርባት ምድር ምቹና ምክንያታዊ ተግባቦት ያየለባት ትሆናለች ብዬ አስባለሁ። እንደ እኔ እይታ
በክፍል ውስጥ "የጎበዝና የሰነፍ" ልዩነት የሚፈጠረው፣ 1) ለሚማሩት ትምህርት ትኩረት የመስጠትና ያለመስጠት ጉዳይ ሆኖ እንጂ ልዩ ተፈጥሮ ኖሯቸው ነው ብዬ አላስብም፣ 2) ብዙ ጊዜ በኛም ሃገር ያለው የትምህርት አሰጣጥ የማስታወስ ችሎታን የሚገመግምና በዛ የሚፈርጅ እንጂ የመረዳት አቅምን የሚጠይቅ ነው ብዬ አላስብም። ለዚህ የኔን ምሳሌ ልስጥ Physics በሆነ አመት ከነ bonusኡ 107 አምጥቼ አውቃለሁ፣ በሆነ አመት ደግሞ ቦነስም ኖሮት 10ማርክ ተጨምሮልኝ 68 አምጥቼ አውቃለሁ። የሁለቱም ውጤቶች ልዩነት፣ 1) ትኩረት ሰጥጬ አጥንቼና ለፈተናው ደግሞ ሸምድጄ ነበር፣ 2) ትኩረት አለመስጠቴና የፈተና ሰሞን ማስታወስ አለመቻሌ ነበር። ከዚህ የተረዳሁት ሌሎች እንደሚሉት "እኔ gifted ተማሪ" ሳልሆን "ለሰው ሃብቱ ትጋቱ" እንዲል ማንኛውንም መፅሐፍ እያንዳንዱ ሰው ትኩረት ሰጥቶ ቢያነበው ይረዳል። በአንዴ ካልተረዳውም ደግሞ ቢያነበው ይረዳዋል። ብዬ አስባለሁ።(በእርግጥ ይህ anecdotal evidence ቢሆንም እስኪ አንዴ የትልቅ ሳይንቲስቶችን ተሞክሮ ዘወር ብለን እንይ። አንስታይን በቴክኒክና ሙያ ነበር የተማረው፣ ኤድሰን በግል ንባብ ነው ያንን የፈበረከው፣ ኒውተን ቤት ውስጥ በ quarantine ጊዜ ነበር ግኝቱን በንባብና በማስረጃ ያገኘው፣...)
(ከgoogle ነው imageኡ)
#ይቀጥላል

Yeshitla Yigezu
122 viewsMoses Daniel, 23:10
Open / Comment