Get Mystery Box with random crypto!

ክፍል 2፣ ምክንያታዊነት(being reasonable) የሰውነት ትልቁ መገለጫ ነው:: “...ሰ | 𝗖𝗵𝗿𝗶𝘀𝘁𝗶𝗮𝗻𝘀 𝗣𝗲𝗿𝘀𝗽𝗲𝗰𝘁𝗶𝘃𝗲𝘀 Archives

ክፍል 2፣

ምክንያታዊነት(being reasonable) የሰውነት ትልቁ መገለጫ ነው::

“...ሰውን እንዲያስብ ልታደርግ ባትችልም፣ ማሰብ እንደሚችል ግን ልትነግረው ትችላለህ...” ከ‘ጥበብ ከጲላጦስ’ መፅሐፍ የተወሰደ። የሰው ልጆች መሆናችን የምንከተለውን፣ የምናምነውን፣ የምንፈልገውን ልንጠይቅ፣ ልናስብ፣ ልንመረምር ይገባል እላለሁ። የአለመኖር መፅሐፍ ደራሲ ዶ/ር ዳዊት በመፅሃፉ ባለው ገፀባህሪ እንዲህ ይለናል፣ “...‘ሰው በአጠቃላይ፤ የኛ ሃገር ደግሞ በተለይ፤ ለመኖር የተባለውን የሚቀበል ነው። ብዙ አይጠይቅም።’...” ለምን ይህ ይሆናል? ለምን በልዩነት ሃገሬ ላይ ይሄ አለመጠየቅና አለመመርመር በዛ? በኃላ ገፅ 107 ላይ እንዲህ ብሎ ወጣቶችን ይመክራል፣ “...በወጣትነትህ አንተ ላይ ያለው ሃላፊነት፤ ስለተባሉትና ስለተፃፉት ነገሮች ማሰብ ብቻ ነው...” መጠየቅ፣ማሰብ....

በዚህ ክፍል የምንዳስሰው፦ ሙግት፣ የሙግት ነጥብ፣ ድምዳሜ፣ አዋጅ፣ ምንጨታዊ ሙግት፣ መስተጋብኣዊ ሙግት፣ ርቱዕ ሙግት፣ ስሙር ሙግት፣ራስን በራስ የሚቃወም ሙግት፣ ተፋልሶ ምን እንደሆኑ በጥቂት ማብራሪያ እናያለን።(ከላይ የተጠቀምኳቸው አብዛኛዎቹ የስነ አመክንዮ ቃላትና ሃረጎችን የተዋስኩት ከዶ/ር ተስፋዬ ሮቤሌ “ስነ አመክንዮ” ከሚለው መፅሐፋቸው ነው። እንድታነቡት በትህትና እጋብዛችኀለሁ።)

#ሙግት(argument) ውበት ባላቸው አረፍተነገሮች የተዋቀረ፣ የመነሻ ነጥቦችና ድምዳሜ የተሰናሰለ ፍልስፍናዊ ውቅር ነው። ሙግት ሃሳባችንን በምክንያት የምንዘውርበት መንገድ ነው። ሙግት መደማመጥ የበዛበት የጠይቂዎች ሜዳ ነው። ሙግት ጭቅጭቅ፣ስድብ፣ እንካ ሰላንቲያ አይደለም። #የሙግት ነጥብ(premise) የእውነትነት ይዘት ያላቸው ድምዳሜውን የሚደፍፉ አ/ነገሮች ናቸው።#ድምዳሜ(conclusion) እውነትነት ያለው በሙግት ነጥቦቹ የሚደገፍ ወይም ስሙምነት ያላቸው አ/ነገሮች ናቸው።#አዋጅ(proposition) የእውነት ፈይዳን(truth value) ያቀፈ ማለትም እውነት ወይንም ሃሰት ሊሆን የሚችል አ/ነገር ነው።#ስሙር ሙግት(valid argument) በአሰካክ ሂደት የሙግት ነጥቡ የድምዳሜውን ሲያፀና(በዋናነት አሰናሰሉ ነው ሚታሰበው)።#ርቱዕ ሙግት(sound argument) የምንለው ደግሞ ምክኖዮኣዊ ስሙር ሲሆንና እውነት የሆኑ የሙግት ነጥቦች ሲኖረው ነው።#ምንጨታዊ ሙግት (deductive argument) የሙግት መነሻ ነጥቦች እውነትነት ለድምዳሜው እውነትነት ዋስትና ሲሰጠን ሙግቱን DA እንለዋልን። “the premises guarantee the truth of their conclusions.”Dr. William Lane Craig.#መስተጋብኣዊ ሙግት(Inductive argument) ከተቀናቃኝ ሙግቶች በላይ የሙግት ነጥቦቹ የድምዳሜውን እውነትነት ደረጃ ሲጨምሩ IA እንላቸዋልን።(የፍልስፍና ት/ት ቅፅ 1 ላይ፣ “ፍራንሲስ ቤከን...አርስቶትልን እንደወረደ ከመቀበልና DA ከመጠቀም ይልቅ የሙከራ ሳይንስን...እና IA
መጠቀም ተፈጥሮን ይበልጥ ለማወቅ እንደሚረዳ ተከራከረ...” ይሉናል። ከሆነ IA ያገኘው ፍራንሲስ ቤከን ነው።)#ራሱን በራስ የመቃወም ሙግት (self-defeating argument) ይህ ሙግት እየተቃወሙ ያሉትን ሃሳብ በግልፅም በውስጠ ታዋቂነትም መደገፍ፣ እየደገፉ ያለወንም ሃሳብ በግልፅም በውስጠ ታዋቂነትም መቃወም። #ተፋልሶ(fallacy) የሙግት ህፀፅ ማለት ሲሆን ብዙና ልዩልዩ ናቸው።

ከፍልስፍና ሀሁ መፅሐፍ የተወሰደ፣ “...ሶቅራጠስ ይጠይቃል፣ ከዚያም መልስን ያገኛል...” እንጠይቅ፣ እውነትን እንከተል። ይቀጥላል...

Yeshitla Yigezu