ክፍል 3፣ #የሺጥላ ይገዙ ምክንያታዊነት የሰውነት ትለቁ መገለጫ ነው:: #ራስን በራስ የመቃወም ሙግት(self-defeating or self-stultifying or self-refuting argument):- በግልፅም ሆነ በውስጠ ታዋቂነት እየደገፉ/እየተቃወሙ ያሉትን ሙግት መቃወም/መደገፍ። #ለምሳሌ1፦ ሁሉም ሰው ውሸታም ነው። >>ይህ አ/ነገር እውነት ከሆነ፦ ራሱን ትክክል አድርጓልና ስህተት ነው። ውሸት ከሆነ የእውነት ፋይዳ ያለው አ/ነገር ሆኗልና ሁሉም ሰው ወሸታም አለመሆኑ አ/ነገሩን ውሸት ያደርገዋል። #ምሳሌ2:- ፍፁም እውነት የለም። ወይንም እውነት ሁሉ አንፃራዊ ነው። 1) ይህ አ/ነገር እውነት ከሆነ፦ ከሱ ጋር እንድንስማማ ይህ ፍፁም እውነት ነው ተቀበሉት እያለን ስለሆነ ስህተት ነው። 2) ውሸት ከሆነ፦ የእውነት ፋይዳ ያለው አ/ነገር ስለሆነ ውሸት ነው። #ምሳሌ3:- እውነት በውጤቱ ይረጋገጣል። ችግሩ፦ አ/ነገሩ እራሱ ስላልተረጋገጠ ውሸት ነው። ወይንም ገና ጅማሬው ላይ ሆኖ ፍፃሜው ላይ ነኝ እያለ ስለሆነ ዋሽቷል።(a means justifies an end እንጂ ተቃራኒው እውነት አይሆንም።) #ምሳሌ4:- ሁሉም ነገር በአምስቱ የስሜት ህዋሳት ካልተረጋገጠ ውሸት ነው። ችግሩ፦ ይህ አ/ነገር እራሱ በአምስቱ የስሜት ህዋሳት ሳይረጋገጥ እውነት እንደሆነ ማሰቡ። #ምሳሌ5:- በአምስቱ የስሜት ህዋሳት የማይረጋገጥ ነገር ሁሉ ትርጉም አልባ ነው። ችግሩ፦ ይህ አ/ነገር በአምስቱ የስሜት ህዋሳት የተረጋገጠ ስላልሆነ ትርጉም አልባነቱን ራሱ በራሱ ላይ መናገሩ። #ምሳሌ6:- ስለ ምንም ነገር እርግጠኛ መሆን አንችልም። ችግሩ፦ ስለ ምንም ነገር እርግጠኛ መሆን አንችልም ስላለው አ/ነገር እርግጠኛ መሆኑ ራሱን በራሱ ይቃወማል። #ምሳሌ7:- ሁሉም እምነት ውሸት ነው። ችግሩ፦ በመሰረቱ ይሄን አ/ነገር ባያምነውና እርግጠኛ ባይሆንበት እንድንቀበለው አያውጅም።(“...the tradition or standard definition of propositional knowledge is the view that knowledge is justified true belief...” Dr. William Lane Craig) ስለዚህ አ/ነገሩንም ጨምሮ ውሸት ሊሆን ነው ይህ ከሆነ ሰህተት ነው። ራሱን በራሱ እየተቃወመ ነው። #ምሳል8:- ስለ ፈጣሪ መኖር/ህላዌ ማወቅ አንችልም። ችግሩ፦ ስለ ፈጣሪመኖር ማወቅ አለመቻሉን ማወቁ ራሱን በራሱ የሚቃወም ሙግት ነው። #ምሳሌ9:- ሰለማምነው እምነት ምንም ማስረጃ ማቅረብ አይጠበቅብኝም። ችግሩ፦ ማስረጃ ማቅረብ እንደማይጠበቅበት ለማስረዳት ማስረጃ ማቅረቡ። #ምሳሌ10:- ስለ ፈጣሪ መኖር ትሩጉም በሚሰጥ አ/ነገር ማውራት አንችልም። ችግሩ፦ ስለ ፈጣሪ መኖር ትርጉም በሚሰጥ አ/ነገር ማውራት አለመቻሉን ትርጉም በሚሰጥ አ/ነገር ስለ ፈጣሪ ማውራቱ። ...ይቀጥላል... 215 viewsMoses Daniel, 21:30