🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ምክንያታዊነት የሰውነት ትልቁ መገለጫ ነው፤ ምክንያታዊነት፦ ሰዎች እንደመሆናችን ከእንስሳት የምን | 𝗖𝗵𝗿𝗶𝘀𝘁𝗶𝗮𝗻𝘀 𝗣𝗲𝗿𝘀𝗽𝗲𝗰𝘁𝗶𝘃𝗲𝘀 Archives

ምክንያታዊነት የሰውነት ትልቁ መገለጫ ነው፤
ምክንያታዊነት፦ ሰዎች እንደመሆናችን ከእንስሳት የምንለይበትና ክቡር ፍጡራን መሆናችን የሚንፀባረቅበት መንገድ ነው። ዶ/ር ተስፋዬ ሮቤሌ ስነ አመክንዮን እንዲህ ይፈቱታል፣ “ሥነ አመክንዮ ትክክለኛውን ሙግት ትክክለኛ ካልሆነ ሙግት የምንለይበት መርሖና ዘዴ፣ ምን እንደ ሆነ የሚያስተምረን የትምህርት ዘርፍ ነው።” እንዲሁም ይህ የትምህርት ዘርፍ የቀናውንና ስሁት የሆነውን ሃሳብ የምንመረምርበት፣ አመለካከታችንንና እምነታችንን በማስረጃና ተገቢ አ/ነገሮችን በመጠቀም ለሰዎች የምናቀርብበት፣ እይታችንን ለዛ ባለው መልኩ ማለትም ሊገመገም፣ሊተችና ተቀባይነት እንዲኖረው አድርገን የምናሰናዳበት ተግባቦት ከሳ("ሳ" ሲጠብቅ)ች ስልት ነው።

#ታላቁ ፈላስፋ አርስጣጣሊስ፣ ልክ አይሳክ ኒውተን የስበትን፣ የእንቅስቃሴንና የባለበት መቆምን ህግ እንዳገኘ(discover እንዳደረገ)፣ አርስቶትልም የአመክንዮን ህግ እንዳዋቀረ ይነገራል። እነኚህ ህጎች አለመፈብረካቸው(invent አለመደረጋቸው) ይልቁን መገኘታቸው በሰዎች መካከል ከጥንትም የነበሩ
እንደሆነ እና በፈጣሪ መኖር ለምናምን የፈጣሪ ስጦታዎች እንደሆኑ እናስተውላለን። ይህ ከሆነ ደግሞ አየርና ውሃን ለመኖር አስፈላጊ ሆነው በአግባቡ እንደምንጠቀማቸው ሁሉ እነኚህንም የአመክንዮ መርሆች በአግባቡ ልንጠቀማቸው ይገባል።

#የአመክንዮን ህግ መጠቀም ለምን ይጠቅማል?
1) ሃሳባችንን በአግባቡና በማስረጃ አስደግፎ ለሌላው ሰው በትህትና ለማስረዳት፣

2) የአብዛኛውን ሰው አመለካከት ለመገምገምና ያን አመለካከት የምንከተለውም የማንከተለውም ለምን እንደሆነ ምክንያታዊ ሆኖ ለመመላለስ፣

3) ከስሜታዊነት በፀዳ መልኩ የሌላውን ሰው እምነትና አመለካከት ለመመርመር፣ ለመገምገም፣ ለመቀበልና ለመተቸት(ትችት ስድብ አይደለም!)፣
4)ሰዎች በመሆናችን የተለያየ አስተሳሰብ፣አመለካከትና እምነት ስላለን ሊያግባባን የሚችል ብቸኛ "common ground" ስለሆነና ሌሎች የትየለሌ ጠቀሜታዎች አሉት።

#በግል እይታዬ ሰዎች ፈጣሪ የሰጣቸው ግሩም አይምሮ አላቸው። ያን አይምሮኣቸውን በሚገባ ቢጠቀሙት የምንኖርባት ምድር ምቹና ምክንያታዊ ተግባቦት ያየለባት ትሆናለች ብዬ አስባለሁ። እንደ እኔ እይታ
በክፍል ውስጥ "የጎበዝና የሰነፍ" ልዩነት የሚፈጠረው፣ 1) ለሚማሩት ትምህርት ትኩረት የመስጠትና ያለመስጠት ጉዳይ ሆኖ እንጂ ልዩ ተፈጥሮ ኖሯቸው ነው ብዬ አላስብም፣ 2) ብዙ ጊዜ በኛም ሃገር ያለው የትምህርት አሰጣጥ የማስታወስ ችሎታን የሚገመግምና በዛ የሚፈርጅ እንጂ የመረዳት አቅምን የሚጠይቅ ነው ብዬ አላስብም። ለዚህ የኔን ምሳሌ ልስጥ Physics በሆነ አመት ከነ bonusኡ 107 አምጥቼ አውቃለሁ፣ በሆነ አመት ደግሞ ቦነስም ኖሮት 10ማርክ ተጨምሮልኝ 68 አምጥቼ አውቃለሁ። የሁለቱም ውጤቶች ልዩነት፣ 1) ትኩረት ሰጥጬ አጥንቼና ለፈተናው ደግሞ ሸምድጄ ነበር፣ 2) ትኩረት አለመስጠቴና የፈተና ሰሞን ማስታወስ አለመቻሌ ነበር። ከዚህ የተረዳሁት ሌሎች እንደሚሉት "እኔ gifted ተማሪ" ሳልሆን "ለሰው ሃብቱ ትጋቱ" እንዲል ማንኛውንም መፅሐፍ እያንዳንዱ ሰው ትኩረት ሰጥቶ ቢያነበው ይረዳል። በአንዴ ካልተረዳውም ደግሞ ቢያነበው ይረዳዋል። ብዬ አስባለሁ።(በእርግጥ ይህ anecdotal evidence ቢሆንም እስኪ አንዴ የትልቅ ሳይንቲስቶችን ተሞክሮ ዘወር ብለን እንይ። አንስታይን በቴክኒክና ሙያ ነበር የተማረው፣ ኤድሰን በግል ንባብ ነው ያንን የፈበረከው፣ ኒውተን ቤት ውስጥ በ quarantine ጊዜ ነበር ግኝቱን በንባብና በማስረጃ ያገኘው፣...)
(ከgoogle ነው imageኡ)
#ይቀጥላል

Yeshitla Yigezu