🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

​​#Rophnan #SOST #Lyrics Rophnan Sew Neh Yilal Lyrics የሃገ | Cover Musics & Lyrics♥️♥️♥️

​​#Rophnan
#SOST #Lyrics


Rophnan
Sew Neh Yilal Lyrics


የሃገሬ ልጅ ስም አገኘሽ ወይ?
የሃገሬ ልጅ ማነኝ አልሽ ይሆን?
እኔስ ልቤ እውነት አየ
ማን እንደሆንኩኝ ለየ
ነህ የተባልኩት እንዲገባኝ
ኋላዬን ዞር ብየ ብቃኝ
ስሜ ተጽፎ አየሁት በክብር ቃል
ሰው ነህ ይላል
ሰው ነህ ይላል
ሰው ነህ ይላል
ከቋንቋ በፊት ከዘር ቀድሞ ተጽፏል
ሰው ነህ ይላል
ሰው ነህ ይላል
ሰው ነህ ይላል
ከሃይማኖት ባህል ከእምነትም ይቀድማል
ሰው ነህ ይላል
ቀድሞ ስላሴን ሸዋ ምኒልክ ተዎድሮስ ሳይቀድም
ግራኝ ሳይከትም ጉዲት ሳትጥል በቁም አክሱምን
ቀድሞ ቢላልን ቀድሞ አዛኑን ነብይ መላኩን
ቀድሞ ያሬድን ሶስቱ ዝማሬን በልጅ መዳንን
ንግስተ ሳቢት ሳትይዝ ስንቋን ለሲና የሚሆን
ሳትጓዝ ልታይ የአምላክን ስራ ጥበብ ሰለሞን
ጠቢቡም ሳይዘምም ምኒልክ ሳይቀድም ጽላት ሳይከተል
ከሁሉ በፊት በሃገሬ ኧረ ማን ነበር አለሜ
ጦቢያ እናት አለም የአልም ብርሃን
ግዮን ሚዞርሽ የነብስ እጣን
ሙሴ ለዮቶር ልጅ የበቃብሽ
ቅድሚያ እሱ ነው ነጻ የወጣብሽ
ምድርም ታሪኳ ቢዘረጋ
ሀ ብሎ ሚጀምር ዘፍጥረት አንቺ ጋር
እምነት ታሪኳ ቢጻፍላት
በአንድነት ተገኙ ናጋሽ እና ጽላት
ዛሬ አንተ ሰው ማነህ? አንተ ሰው ማነህ? ብለው ጠየቁኝ
የማነኝ ልበል ከአንቺ መፈጠር ብዙ አድርጎኝ
ያ ሰው ስም ያውጣ ያውቅበታል
የልጁ ማገር ነው የአባት ቤት ይመታል
ያ ሰው ስም ያውጣ ያውቅበታል
የልጁ ሰው መሆን የአባቱ ይበቃል
የሃገሬ ልጅ ስም አገኘህ ወይ?
የሃገሬ ልጅ ማነኝ አልክ ይሆን?
እኔስ ልቤ እውነት አየ
ማን እንደሆንኩኝ ለየ
ነህ የተባልኩት እንዲገባኝ
ኋላዬን ዞር ብየ ብቃኝ
ስሜ ተጽፎ አየሁት በክብር ቃል
ሰው ነህ ይላል
የእናቴ መቁጠሪያ ዞር ዞር
የወጣው ልጇ ሰላም ጤና እንዲሆን
በይ እናት አለም ጸሎትሽን ከእኔ ላይ ቀንሰሽ ለኢትዮጵያ አድርጊ
እኔ እንድኖር አለዚያማ ቢደርስልኝ የአንቺ ጸሎትእማ
ለብቻየ ያለሃገር እማ አልኖርማ
አንቺ ያየሽውን አላይማ
እውነት እውነት ጸሎትሽ ላይ ሃገር ጨምሪበት
የኔ ትውልድ ሰው እንዳይሆንበት
አጎንብሶ ሄደ ከአንገትና ጀርባው ዘር ጭነውበት
አይቸ እንዳላየሁ ሆድ ከሃገር ይሰፋል ብየ እያለፍኩት
ማነህ? ብለው እነ ሆድ ከሃገር ይበልጣል ልቤን አስጨነቁት
ያ ሰው ስም ያውጣ ያውቅበታል
የልጁ ማገር ነው የአባት ቤት ይመታል
ያ ሰው ስም ያውጣ ያውቅበታል
የልጁ ሰው መሆን የአባቱ ይበቃል
ሰው ነህ ይላል
ሰው ነህ ይላል
ሰው ነህ ይላል
ሰው ነህ ይላል
ሰው ነህ ይላል
ሰው ነህ ይላል
ባላገርነት ይህ ነው
ሰው ሃገሩ እግዚአብሄር ነው
እግዜር ሃገሩ ፍቅር
ፍቅር ግን የለው ሃገር
ፍቅር ሳይኖረው ሃገር
ሃገሬ አንቺን ሳፈቅር
የፈጠረኝ እንዳለው ሰው አታደርጊኝ ምነው
የፍቅር ቃል አያልፍ ዘንድ አለም ያልፋል
ከአንቺ በፊት ነበር ስሜ ሰው ነህ ይላል
ፍቅር ሳይኖረው ሃገር
ሃገሬ አንቺን ሳፈቅር
ለፍቅር ቦታ ከሌለሽ ከበር እግዜርን መለስሽ
እግዜርን መለስሽ


Lyrics By @Jo_Ynwa


For More Join Us @cover_musics