🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

​​#Rophnan #SOST #Lyrics Rophnan Sew Weys Hager Lyrics ጥያ | Cover Musics & Lyrics♥️♥️♥️

​​#Rophnan
#SOST #Lyrics


Rophnan
Sew Weys Hager Lyrics


ጥያቄ ከአለም በፊት ከሃገር እና ሰው
በፈጠረን ፊት ሚበልጥ ማነው?
ጥያቄ በፈጠረን ፊት ከበለጠ ሰው
እንደአምላክ ባስብ ስህተቱ የት ነው?
ጥያቄ የቱን ባስቀድም ሰው ወይስ ሃገር
የሃገሬ ነገር ይሞላ ነበር?
ጥያቄ ሃገሬን ሃገር ካደረገማ
ሰውን ላስቀድም ሰው ልሁንና
እንደአድዋ እንደዚያ ሰሞን
ሃገሬ አማረች ሰው ለሰው ሲሆን
ለካ አድዋ ለሰው ልጅ ነበር
ለነጻነቱ የሆነው ሃገር
አሉ ምኒልኩ
መልእክቱን ሲልኩ
አሉ ምኒልኩ
መልእክቱን ሲልኩ
ሚስትህን ሚቀማህ
ማተብህን ሚያወልቅ
ልጅህን ሊወርሰው
ማንነት ሊያርቅ
ባርያው ሊያረግህ
ቁሟል ከደጅህ
ሃገርህ ሚስትህ ናት ደግሞም እናትህ
ሃገርህ ልጅህ ናት ደግሞም ማተብህ
ሰው ሆይ ተከተለኝ ሰው አርገኝ ላርግህ
ሰው አርገኝ ላርግህ
እናስ ይህ ምን ይላል?
ሃገር ሲተነተን የሰው ልጅ ይሆናል
ይሆናል አድዋን ለሃገር ያደረገው ማነው?
አድዋ ለሰው ልጅ አድዋ ለኔ ነው የኔ ነው
ሚስትህም ትሁን እናት ልጅም ማለት ሁሉም ሰው
የሂጃብም የማህተብም ተስፋው ማሰሪያው ሰው ነው
ድንግሏም እርሱም የሰው ልጅ
ሰው ጠልተው ማህተቡን ላይበጅ
ሰው ላፍቅር ጀኛ ልሁንና
ልቤ ላይ ነው የዛሬ አድዋ
ሰከላ አባይን ወለደች
እናቴም እኔን
አድዋ ከራስ ጀመረ እራሱን ያሸነፈ
ለሰው ተረፈ
ሁሉም ትውልድ አድዋ አለው
የኔም አድዋ ልቤ ላይ ነው
ጀግና ማለት ይቅርባይ ነው
ቂም በሆዱ ከሰበቀ
ጎጃም ሰው ካላረቀ
ከይቅርታ ከራቀ
በላይ መቼ ዘለቀ
ይቅር ካላወቅንማ
ዮሃንስ ለሃገር ወድቆ ሲሰዋ
ቴወድሮስ መቅደላ የጠጣት ጽዋ
ለከንቱ ነዋ
ባልቻ ዛሬም ይነፍሳል
አሉላ ዛሬም ይደርሳል
ቃል እየተማዘዝነ
እኛው በኛው አንሰን ከተራከስነ
በእነሱ አድዋ ድል አርገናል
ግን የኛን አድዋ ተሸንፈናል
ተው...
አድዋን ለሃገር ያደረገው ማነው?
አድዋ ለሰው ልጅ አድዋ ለኔ ነው
ሁሉም ትውልድ አድዋ አለው
የኔም አድዋ ልቤ ላይ ነው
ጀኛ ማለት ዛሬ ዛሬ ይቅር ባይ ነው
ሰከላ አባይን ወለደች
እናቴም እኔን!
ሰከላ አባይን ወለደች
እናቴም እኔን!


Lyrics By @jo_ynwa


For More Join Us @cover_musics