2022-06-19 14:12:41
" ከሊቨርፑል ጋር ብዙ ዋንጫዎችን ማሸነፍ እፈልጋለው "
የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ውዱ ፈራሚ ዳርዊን ኑኔዝ ለቀያዮቹ ፊርማውን ካኖረ በኋላ ተከታዩን አስተያየት ሰጥቷል ።
" ሊቨርፑልን በመቀላቀሌ ደስተኛ ነኝ ፤ ሊቨርፑልን በተቃራኒው ገጥሜያለው በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ላይ የቀያዮቹን ብዙ ጨዋታ ተመልክቻለው የሊቨርፑል የጨዋታ ዘይቤ ከእኔ ጋር ይሄዳል ።
ትላልቅ ተጫዋቾች እዚህ ይገኛሉ ፤ የሊቨርፑል የልምምድን ማዕከል ስመለከት በመሰረተ ልማቶቹ ተገርሜያለው ።
ለሊቨርፑል ፊርማዬን ካኖርኩባቸው አንዱ ምክንያት ዋንጫዎችን ለማሸነፍ ነው ፤ ከሊቨርፑል ጋር ብዙ ዋንጫዎችን ማሸነፍ እፈልጋለው " ሲል ተደምጧል ።
በሊቨርፑል ዳርዊን ኑኔዝ 27 ቁጥር ማሊያን እንደሚያደርግ ተገልጿል ።
@Ethio_Liverpools
571 views11:12