🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

አርጦግሮል ኢትዮ

Logo of telegram channel dirilis_ertugrul_et — አርጦግሮል ኢትዮ
Logo of telegram channel dirilis_ertugrul_et — አርጦግሮል ኢትዮ
Channel address: @dirilis_ertugrul_et
Categories: Videos
Language: English
Subscribers: 153

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


The latest Messages

2022-07-01 19:35:04
ሊቨርፑል የኮከቡን ውል አራዘመ !

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል የግብፃዊውን ኮከቡን ሞሀመድ ሳላህ ውል ለተጨማሪ ዓመታት ማራዘማቸውን ይፋ አድርገዋል ።

ሞሀመድ ሳላህ በሊቨርፑል ቤት ለተጨማሪ ሶስት ዓመታት በመርሲሳይድ ለመቆየት መስማማቱ ይፋ ተደርጓል ። በሳምንት 350ሺህ ፓውንድ የሚያገኝ ይሆናል።

@Ethio_Liverpools
468 viewsedited  16:35
Open / Comment
2022-06-25 10:04:09
ሊቨርፑል ከተጫዋቹ ጋር ሊለያይ ይችላል !

የሊቨርፑሉ ግብፃዊው የፊት መስመር ተጫዋች ሞሀመድ ሳላህ የክረምቱ የዝውውር መስኮት እስኪጠናቀቅ ድረስ ኮንትራቱን የማያራዝም ከሆነ ቀያዮቹ ተጫዋቹን የመሸጥ ፍላጎት እንዳላቸው ተገልጿል ።

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ሞሀመድ ሳላህ የጠየቀውን የተጋነነ ሳምንታዊ ደሞዝ የመክፈል ፍላጎት እንደሌላቸው መግለፃቸው ይታወሳል ።

ሊቨርፑል ለሞሀመድ ሳላህ 60 ሚሊዮን ፓውንድ የዝውውር ሂሳብ ከቀረበላቸው ተጫዋቹን የመሸጥ ፍላጎት እንዳላቸው ተነግሯል ።

@Ethio_Liverpools
798 views07:04
Open / Comment
2022-06-23 11:59:05
ሞሀመድ ሳለህ ላደገበት መንደር !

ግብፃዊው ኮከብ የፊት መስመር ተጫዋች ለትውልድ መንደሩ የተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል ።

ሳላህ ተወልዶ ላደገበት ናግሪግ መንደር ሆስፒታል ፣ ትምህርት ቤት እና የወጣቶች ማዕከል አስገንብቶ አስረክቧል ።

ሳላህ በችግር ላይ ለሚገኙ ቤተሰቦቹ በየወሩ 3,500 ዶላር ድጎማ እንደሚያደርግ ተዘግቧል ።

ሳላህ የኮቪድ ወረርሽኝ በተከሰተበት ወቅት በሺዎች የሚቆጠር የምግብ አቅርቦት ከ 500ሺህ ዶላር በላይ መለገሱ ተነግሮለታል ።

ሳለህ በተለይም በ 2019 በግብፅ ለካንሰር ታማሚዎች የሚውል 2.5 ሚልዮን ዶላር እርዳታ ማድረጉ ተገልጿል ።

@Ethio_Liverpools
775 views08:59
Open / Comment
2022-06-23 08:09:25
"ለእኔ ሁሉንም ነገር ለማሳካት ትክክለኛው ጊዜ እና ትክክለኛው ክለብ ነበር!" ሳዲዮ ማኔ ከክለቡ ጋር ባደረገው የስንብት ቃለ ምልልስ እንዴት ሊቨርፑልን ለመቀላቀል እንደወሰነ እና ለምን እንደለቀቀ ታሪኩን ተናግሯል።

via LFCTV

[ Sky Sports ]
@Ethio_Liverpools
626 views05:09
Open / Comment
2022-06-22 13:13:06
ሊቨርፑል ከተጫዋቹ ጋር ሊለያይ ነው !

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ጃፓናዊውን ተጫዋቹን ታኩሚ ሚናሚኖ ለመሸጥ ከስምምነት ላይ መድረሳቸው ተገልጿል ።

ሞኖኮ ተጫዋቹን ለማስፈረም ከስምምነት የደረሰው ክለብ ሲሆን ለዝውውሩ አስራ ስምንት ሚልዮን ፓውንድ እንደሚያወጡ ተዘግቧል ።

የ 27 ዓመቱ ታኩሚ ሚናሚኖ በግል ጉዳዮች ላይ ከሞናኮ ጋር ሲስማማ የእረፍት ጊዜውን በሀገሩ ጃፓን እያሳለፈ መሆኑን ተከትሎ በቀጣይ ቀናት የህክምና ምርመራውን በማድረግ ዝውውሩ ይፋ እንደሚደረግ ተገልጿል ።

ታኩሚ ሚናሚኖ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ለሊቨርፑል በአስራ አንድ ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ መጫወት ችሏል ።

@Ethio_Liverpools
668 views10:13
Open / Comment
2022-06-20 21:11:40
የሳድዮ ማኔ ዝውውር መጠናቀቁ ተገለፀ !

ሴኔጋላዊው የሊቨርፑል የመስመር ተጫዋች ሳድዮ ማኔ ወደ ባየር ሙኒክ የሚያደርገው ዝውውር የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝ ይፋ ተደርጓል ።

ሳድዮ ማኔ ሶስት ዓመታትን በሙኒክ የሚያቆየውን ውል በሁለቱ ክለቦች መካከል ከስምምነት መደረሱ ተዘግቧል ።

በነገው ዕለት ሳድዮ ማኔ የህክምና ምርመራውን በሙኒክ የሚያካሂድ ሲሆን እሮብ በይፋ ትውውቅ እንደሚያደርግ ታውቋል ።

https://t.me/+ZAjTqjebfvFjMTVk
728 views18:11
Open / Comment
2022-06-19 14:12:54
ሊቨርፑል ካልቪን ራምሴን አስፈርሟል !

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ስኮትላንዳዊውን የመስመር ተከላካይ ካልቪን ራምሴን ከአበርዲን እስከ 2027 በሚቆይ የኮንትራት ውል ማስፈረማቸውን ተገልጿል ።

የአስራ ስምንት አመቱ ስኮትላንዳዊው የመስመር ተከላካይ በ 6.5 ሚሊዮን ፓውንድ ቀያዮቹን የተቀላቀለ ሲሆን በአንፊልድ የሚያቆየውን የአምስት አመት ኮንትራት መፈረሙ ተዘግቧል ።

@Ethio_Liverpools
@Ethio_Liverpools
829 views11:12
Open / Comment
2022-06-19 14:12:45
ሳዲዮ ማኔ ወደ ባየር ሙኒክ !

ባየር ሙኒክ የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ሴኔጋላዊውን የፊት መስመር ተጫዋች ሳዲዮ ማኔን ለማስፈረም ከስምምነት ላይ መድረሳቸው ይታወሳል ።

የጀርመኑ ክለብ ባየር ሙኒክ በይፋ የፊታችን እሮብ በአልያንዝ አሬና ሴኔጋላዊውን የፊት መስመር ተጫዋች ሳዲዮ ማኔን አዲሱ የክለባቸው ተጫዋች አድርገው ለማስተዋወቅ እቅድ መያዛቸው ተዘግቧል ።

@Ethio_Liverpools
750 views11:12
Open / Comment
2022-06-19 14:12:44
የሞሀመድ ሳላህ ጉዳት !

በእንግሊዝ ኤፍ ኤ ካፕ የፍፃሜ ጨዋታ ላይ ሞሀመድ ሳላህ ካጋጠመው ጉዳት ሙሉ ለሙሉ ለማገገም እስካሁን እንዳልቻለ የግብፅ ብሄራዊ ቡድን ዶክተር ገልፀዋል ።

ሞሀመድ ሳላህ ፈርኦኖቹ ኢትዮጵያ ጋር ካደረጉት የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ ውጪ የሆነው በጭኑ ላይ ከደረሰበት ጉዳት በአግባቡ ባለማገገሙ መሆኑን ገልፀዋል ።

@Ethio_Liverpools
608 views11:12
Open / Comment
2022-06-19 14:12:44
ሊቨርፑል የተጫዋቹን ኮንትራት ማራዘም ይፈልጋል !

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል እንግሊዛዊው የመሀል ተከላካይ ጆ ጎሜዝ በ 2024 የውድድር አመት መጨረሻ ከሊቨርፑል ጋር ያለው ኮንትራት ይጠናቀቃል ።

አስቶን ቪላ እና ኒውካስትል ተጫዋቹን የማስፈረም ፍላጎት ቢያሳዩም ሊቨርፑል የቅድመ የውድድር አመት ዝግጅታቸውን በሚያደርጉበት ወቅት ለተጫዋቹ የውል ማራዘሚያ ኮንትራት ለማቅረብ መዘጋጀታቸው ተዘግቧል ።

ባሳለፍነው የውድድር አመት ጆ ጎሜዝ ለሊቨርፑል በአስራ አንድ ጨዋታዎች ላይ ብቻ በቋሚ አሰላለፍ ውስጥ ገብቶ መጫወቱ ይታወሳል ።

@Ethio_Liverpools
571 views11:12
Open / Comment