🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

አንድ ጎዳና ላይ ሰርከስ የሚያሳይ አርቲስት በፖሊስ መኮንን በተገደለባት ደቡብ አሜሪካዊት ሀገር ቺ | DW Amharic

አንድ ጎዳና ላይ ሰርከስ የሚያሳይ አርቲስት በፖሊስ መኮንን በተገደለባት ደቡብ አሜሪካዊት ሀገር ቺሊ ውስጥ ከፍተኛ አመጽ ተቀሰቀሰ። በሀገሪቱ የሰዓት አቆጣጠር ዓርብ ማምሻውን በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ቁጣቸውን ለመግለፅ በደቡባዊ ቺሊ አደባባይ ወጥተዋል። እንደ መገናኛ ብዙሃን ዘገባ ሰልፈኞች አንድ የመንግሥት መሥሪያ ቤት እና መኖሪያ ቤቶችን በእሳት አጋይተዋል። ከዚህም ሌላ መንገዶችን በመዝጋት በፖሊስ ጣቢያ ላይ ጥቃት አድርሰዋል። ሰልፈኛውን ለመበተን የፀጥታ ኃይሎች አስለቃሽ ጭስና ውኃ መጠቀማቸውም ተጠቁሟል። የሰርከስ አርቲስቱ የተገደለው በከተማ መሃል ቁጥጥር የሚያካሂዱትን ሁለት ፖሊሶች ትዕዛዝ ተላልፏል በሚል ነው። ፖሊስ የመኮንኑን ርምጃ ትክክል ነው በሚል የደገፈ ሲሆን ጉዳዮን ለማጣራት አቃቤ ሕግ ምርመራ መጀመሩን አስታውቋል። የቺሊ ፖሊስ ብዙውን ጊዜ ጭካኔ በተሞላው ባህሪ ምክንያት በተደጋጋሚ ከፍተኛ ወቀሳ እንደሚቀርብበት የጀርመን የዜና ወኪል ዘግቧል።