Get Mystery Box with random crypto!

ጥር 30፣2013 አርዕስተ ዜና -ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ ያስገነባችዉን ግድብ፣ ሱዳንና ግብፅ | DW Amharic

ጥር 30፣2013
አርዕስተ ዜና
-ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ ያስገነባችዉን ግድብ፣ ሱዳንና ግብፅን ሳታማክር ዉኃ እንዳትሞላ ሱዳን አስጠነቀቀች።የሱዳኑ የዉኃ ሚንስትር እንደሚሉት ኢትዮጵያ በመጪዉ ኃምሌ በተናጥል የሕዳሴ ግድብን ዉኃ ከሞላች ለሱዳን ብሔራዊ ደሕንነት ቀጥተኛ ሥጋት ትጭራለች።የሶስቱን ሐገራት ዉዝግብ ለማስወገድም የዓለም መንግስታትና ማሕበራት ጣልቃ እንዲገቡ ካርቱም ጠይቃለች።

-የዓለም ምግብ ድርጅት በጦርነት ለተጎዳዉ የትግራይ ሕዝብ ርዳታ ለማቅረብ ከኢትዮጵያ መንግስት ፈቃድ ማግኘቱን አስታወቀ።የድርጅቱ የበላይ ኃላፊ እንደሚሉት ድርጅታቸዉ ትራንስፖርት በማይገኝበት አካባቢ ጨምሮ ለሚኖረዉ አንድ ሚሊዮን የትግራይ ሕዝብ ርዳታ ይሰጣል።

-የሶማሊያ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ተራዘመ።ነገ ይደረጋል ተብሎ የነበረዉ ምርጫ የተራዘመዉ ተቀናቃኝ ፖለቲከኞች በመራጮች ማንነትና በምርጫዉ ሒደት ባለመስማማታቸዉ ነዉ።የሶማሊያ ፖለቲከኞች ለስልጣን ሲሻኮቱ አክራሪዉ ደፈጣ ተዋጊ ቡድን አሸባብ 12 የስለላ ባለሙያዎችን ገድሏል።
ዜናዉ በድምፅ ለማድመጥ፣ እዚሕ ይጫኑ https://p.dw.com/p/3p1bs