🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

በቤኒሻጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ሰላምን ለማስፈን እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን ያግዛል የተባለ | DW Amharic

በቤኒሻጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ሰላምን ለማስፈን እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን ያግዛል የተባለለት እና ከወረዳ እስከ ክልል የሚገኙትን አመራሮች ያሳተፈ ጉባኤ በአሶሳ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡ የቤኒንሻል ጉሙዝ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢሳቅ አብዱልቃድር ጉባኤው በመተከል ዞን የጸጥታ ችግርን በዘላቂነት ለመፍታት ያለመ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የመተከል ዞን የጸጥታ ችግርን ለመቅረፍ ወደ ስራ የገባው የተቀናጀ ግብረ ሀይል ወደ ጫካ ሸሽተው የነበሩ 34ሺ የሚደርሱ የጉሙዝ ማህረሰብን ወደ ቀዬአቸው መመለስ መቻሉን ከዞኑ ኮሙኒኬሽን መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ በ151 ቀበሌዎችም የመንግስት መዋቅር በአዲስ መልክ መደራጀታቸውም ተገልጿል፡፡ በተደጋጋሚ የሚከሰተው የጸጥታ ችግርን በዘላቂነት በመፍታት የዜጎች ደህንነት ትኩረት እንዲሰጠው ማድረግ የጉባኤው ዓላማ መሆኑን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢሳቅ አብዱል ቃድር ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል፡፡ በዞኑ የተፈጠረው የጸጥታ ችግር የአመራር ኃላፊነቱን በአግባቡ ባለመወጣቱ የተፈጠረ መሆኑን የተናገሩ ሲሆን በጉባኤው ላይ የማጥራት ስራም ይከናወናል ብለዋል፡፡