Get Mystery Box with random crypto!

የሀገሪቱን ሉዓላዊነት ጥሶ የገባው የሱዳን ጦር የፈጠረው ችግር የበለጠ ከመወሳሰቡ በፊት መንግስት | DW Amharic

የሀገሪቱን ሉዓላዊነት ጥሶ የገባው የሱዳን ጦር የፈጠረው ችግር የበለጠ ከመወሳሰቡ በፊት መንግስት እልባት እንዲፈልግለት ዓለም አቀፍ የአማራ ህብረት የተባለ ማህበር ጠየቀ፡፡
ማህበሩ ትናንት ማምሻውን በሰጠው መግለጫ እንዳመለከተው <<የሱዳን ጦር የአገራችንን ድንበር ተሸግሮ ረጅም ኪሎሜትር ዘልቆ ገብቷል>> ብሏል፡፡ በመሆኑም ችግሮቹ ከመወሳሰባቸው በፊት መንግሰት እልባት መፈለግ አለበት ሲሉ የህብረቱ ጽ/ ቤት ኃላፊ አቶ መሳፍንት መንግስቱ ጠይቀዋል፡፡
ባለፈው ዓመት ከደንቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ታፍነው ተወሰዱ ተማሪዎችን ጉዳይ በተመለከተም መንግስት ይፋዊ መግለጫ እንዲሰጥ ኃላፊው ጠይቀዋል፡፡
ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እና ከወለጋ ዞኖች አካባቢ የተፈናቀሉ ወገኖች ወደ ነበሩበት ከመመለሳቸው በፊት መንግስት አስተማማኝ ዋስትና እንዲሰጣቸውም ህብረት ጨምሮ አሳስቧል፡፡