Get Mystery Box with random crypto!

የሱዳኑ ጠቅላይ ሚንስትር አብደላ ሀምዶክ 7 የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችን በአዲሱ ካቢኔያቸው ውስጥ ማካ | DW Amharic

የሱዳኑ ጠቅላይ ሚንስትር አብደላ ሀምዶክ 7 የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችን በአዲሱ ካቢኔያቸው ውስጥ ማካተታቸው ተነገረ።ጠቅላይ ሚንስትሩ ባለፈው እሁድ የቀድሞዎቹን የካቢኔ አባላት ሚንስትሮችን ከበተኑ በኋላ ተቃዋሚዎችን ያካተቱበትን አዲሶቹን ሚንስትሮች ይፋ አድርገዋል። የተቃዋሚዎችን በካቢኔ አባላት ውስጥ ያካተቱት አብደላ ሀምዶክ ባለፈው ጥቅምት ወር የተደረሰው የሰላም ስምምነት አንድ አካል እንደሆነም ተዘግቧል።አካታች ነው በተባለለት በአዲሱ የሀምዶክ መንግስት ውስጥ ሁለት ሚንስትሮች ከወታደራሩ ቡድን መውሰዳቸውም ነው የተገለጸው። ነጻነት ለለውጥ የተሰኘው ኃይል ስብስብ አባላት የሆኑ እና የኦማር አልበሽርን መንግስት ገዝግዘው በመጣል ውስጥ ትልቅ ሚና ነበራቸው የተባለላቸው ሰዎች የአዲሱን መንግስት አብዛኛውን የካቢኔ ሚንስትርነት ወንበር ይዘዋል።በሹመቱ ውስጥ ከተካተቱት የሱዳን የመጨረሻው በዴሞክራሲያዊ መንገድ ጠቅላይ ተመርጠው የነበሩት ጠቅላይ ሚንስትር ሳዲቅ አል መሃዲ ሴት ልጅ መርዬም ሳዲቅ አል መሃዲ የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሆነው ተሾመዋል። የአብደላ ሀምዶክ አዲሱ መንግስት ሱዳን ወደ ዴሞክራሲያዊ መንገድ ለምታደርገው ጉዞ ሊያግዛት እንደሚችል ዘገባዎች ያመለክታሉ።